ሰላም ጥያቄ ለ ሙስሊሞች ማሳሰብያ 1.ሙስሊም ያሎናችሁ ሰዎች ምንም አይነት አስተያየት አንዳትሰጡ 2. ጥያቄው ለእውቀት እንጂ ሌላ አላማም ምክንያትም ስሌለው በቅንነት እና በእውቀት የተደገፈ ማብራርያ ፈልጋለው አመሰግናለሁ 🙏 1.ሙስሊም ሴቶች የሚለብሱት አለባበስ "ኒቃማ" መሰለኝ ሚባለው ሃይማኖታዊ ጥቅሙ ምንድነው???? 2.ይህን አለባበስ በሃይማኖት ትክክል ነው ብላችሁ ብታስቡ እንኩዋን ማንነትን መደበቅ አደለም ወይ??? የዛ ሃይማኖት ተከታይ ያሎኑ ወንጀለኞች ራሳቸውን ለመደበቅ ቢጠቀሙበት ማነው ተጠያቂ??? 3. መታወቂያ የሚያስፈልጋችሁ ቦታዎች ላይ እንዴት ነው የምታልፉት???? Btw የሙስሊም ሴቶች አለባበስ አድናቂ ነኝ እኔም እራሴ እለብሳለው 😊 ከዚ አለባበስ ውጭ አመሰግናለሁ ክርክር ጭቅጭቅ አደለም ምላሽ ብቻ
Jun 26, 2023ስለ ቅን አወራርሽ እናመሰግናለን። 1, ሙስሊም ነኝ። 2, በቻልኩት መጠን ቅን እና ማስረጃ ያለውን መልስ ለመስጠት እሞክራለሁ። ዓረፋ በደረሰበትና ወዲህ ወዲያ እያልን ባለንበት ሰአት ይህን መጠየቅ 🤦🏽♂ ያስብላል¡ 1. "ኒቃብ" ማለት በቀጥተኛ የዓረብኛ ትርጉሙ መሸፈኛ ማለት ሲሆን ፊትን የሚሸፍን ነው። አላህ ሙስሊም ሴቶችን እንዲሸፋፈኑ ትዕዛዝ ሲሰጥና ምክንያቱን ሲያስቀምጥ እንዲህ ይላል:- "33፥59 አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ *ለምእምናን ሚስቶችም #ከመከናነቢያዎቻቸው _በላያቸው_ላይ_እንዲለቁ_ንገራቸው*፡፡ #ይህ_እንዲታወቁ_እና_በባለጌዎች_እንዳይደፈሩ_ለመኾን_በጣም_የቀረበ_ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡ يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا" ጥቅሙ ይህ ነው። 2. በሐይማኖት ትክክል ከሆነ በሌላው እይታ ትክክል ቢሆንም ባይሆንም ደንታ ሊኖረን አይገባም። ምክንያቱም ወደዚህ ምድር የመጣነው ለቀጣዩ አለማችን እንድንዘጋጅበት ድልድይ ሆኖ ነው። ምሳሌ: ያንቺ እናት እጅግ በጣም ክፉ ነች እንበል.. እናትሽ ክፉ መሆኗ ለሌሎች አባቶች ክፉ እንዲሆኑ በር ይከፍታል? ማለቴ.. #ሙስሊም_የሆነች_ሴት የአላህን ውዴታ ለማግኘት የለበሰችው ልብስና #ሙስሊም_ያልሆነች_ሴት ለወንጀል የለበሰችው ልብስ የሚያገናኘው ነገር የለም። ወደ አውሮጳ ብትሄጂ 80% የሚጠጉ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉ ካህናት በትምህርትና በጸሎት ስም ህጻናትና አዋቂ ሴቶችን እንዲሁም ወንዶችን አስገድደው በመድፈር የሚታሙ ናቸው። ታድያ እኚህ ቆሻሾች ባደረጉት ነውር ኢትዮ ውስጥ ያሉ ካቶሊኮች አስገድዶ ደፋሪ እንዲሆኑ በር ይከፍታል? እኔ ኮፊያ አድርጌ ስርቆት በመፈጸሜ ሌላው ከብርድ ለመከላከል ብሎ ካደረገው ኮፊያ ጋር አንድ አይነት አላማና ፍርድ ይሰጠዋል? እኔ ኮፊያውን ለብሼ በመስረቄ ሌላውም ኮፊያ ለብሶ ይሰርቃል ማለት ነው? አንድ ሰው ለሰራው ጥፋት መወቀስ ያለበት እራሱ እንጂ እናቱ፣ አባቱ፣ ወይም ጓደኛው ሊሆን አይገባም። 3. መታወቂያ ሲያስፈልግ አስገዳጅ ነገር በመሆኑ ፎቶ ተነስተው መታወቂያቸው ላይ ይለጠፋል። በዚህም መታወቂያው ሲፈለግ ማየት የሚገባው ሰው ያየዋል። ያልተመለሰልሽ ጥያቄ ካለ እንቀጥላለን። በዚህ ሰአት አጭር ጊዜ ስላለን ብዙ ለመጻፍ አይመችም።
Jun 27, 2023