Cancer naberabing ena ya beshta bechenkat mekenyat yebesebingal ena fkrainga alaching esua demo metamaman setak eyerakaching hadach kaza giza behuala betam eyebasabing meta mndnw maderag yalabing
Jun 22, 2023ባይገርምህ እኔም የጣፊያ ካንሰር ታማሚ ነበርኩ። ህዳር ወር ላይ ውጭ ሀገር surgery ተደርጎልኝ ፣ ጣፊያዬ ሙሉውን ተቆርጦ ወጥቶ ፣ Adjuvant chemotherapy አድርጌ፣ insulin እየወሰድኩ ነው አሁን በእግዜር ፍቃድ በህይወት ያለሁት። እና ልልህ የፈለኩት በዚህ ሁሉ process ውስጥ ሳልፍ ብዙ ሰዎችን ተዋውቄያለሁ፣ ከብዙዎቹም ጋር ትልቅ የሚባል emotional connection ፈጥሬ ነበር። አንዳንድ ቅርቤ የነበሩ ሰዎችም በቅርቡ ሟች ነው ብለው ጥለውኝ የራቁኝም ነበሩ፣ ለዛውም የደም ዘመዶቼ፤ እኔ ግን ያጣሁትን እያሰብኩ በጭንቀት ተብከንክኜ ሌሎች የሚያስቡልኝም ሰዎች ከማስጨነቅ ይልቅ በተቻለ መጠን Optimist ሆኜ የኋላዬን ሳይሆን የወደፊቴን እያሰብኩ አእምሮዬን በተቻለ መጠን ንፁህ አደርገው ነበር። የoptimismሜም ውጤት ይኸው ሰምሮልኝ ከሞላ ጎደል ጤነኛ ሆኜ እየኖርኩ ነው። እነዛ የራቁኝን ሰዎች እግዜር ይፋረዳቸው። ሰው ቢሄድ ሰው ይመጣል አይዞን፣ እሷ እግር ትብላ - ላንተ ተብላ የተሰራች ምርጥ፣ የምትረዳህ ሴት ወደፊት መገናኘትህ አይቀርም። ታዲያ አንተም ቆፍጠን ብለህ በተቻለ መጠን በoptimism ኑር እንጂ እየተጨነክ እድሜህን አታሳጥር። ከexperience ነው የማወራው ወንድሜ እመነኝ!
Jun 23, 2023