እስኪ ' እየሱስ ' ማነው ብለህ ለማወቅ ሞክር
ያኔ ለምን እንደ ሚትኖር ታውቃለህ!
አንተስ ጤናማ ሰውነት አለህ (ላይሆን ይችላል)
እኔን ግን አስብ ራሰን በጣም ጠላ ነበር በጣም አስቀያሚ ነኝ በዛ ላይ ደግሞ ቁመቴ የ 10 አመት ልጅ ነው ሚያክለው , ድሮ ግድ አይሰጠኝም ነበር ግን እያደኩ ስመጣ (በዕድሜ ብቻ ነው ደግሞ ማድገው😂) እና በቃ 17 አከባቢ ስደርስ በቃ መንቃት ጀመርኩ ራሰን በጣም አንደ ተረገመ ሰው ማየት ጀመርኩ በቃ ስለ ወደፍት ሳስብ ጨለማ ብቻ ነበር የሚታየኝ በቃ ሚስት አላገኝም ደስተኛ መሆን አልችልም ብየ ስቅስቅ ብዬ ማልቀስ ጀመርኩ , በኔ ሁኔታ እንዲያውም ከኔማ የባሰ ሁኔታ ውስጥ ያሉ እንዳሉ አውቃሉ ግን እነሱ እንደነ አያስቡም ምክንያቱም እኔ በጣም ጎበዝ ነበርኩ በት/ት ስለ ነገሮች አውቃለሁ በቃ ግን ራሰን ስለ አንዳንድ ነገሮች መጠየቅ ጀመርኩ
በቃ ደስተኛ መሆን ከተፈጥሮ የሚለገስ ነው?
ይቺ የሚታስጠላ አለም በቃ አንድን ቆንጆ ሀብታም ደስተኛ ታረጋለች ለላውን ደሞ ደሀ አስቀያሚ ታረጋለች?
ብየ ራሰን መጠየቅ ጀመርኩ በቃ በነገሮች ደስተኛ መሆን አልቻልኩም ለምን እንደተፈጠርኩ ራሱ ራሰን መጠየቅ ጀመርኩ , መጨነቅ የዘውትር ስራየ ሆነ ራሰን ለማጥፋት አሰብኩ ግን ስለ ቤተሰቦቼ ብየ ተውኩት!
በቃ የዝህች አለም ስርዐት ብየ የማስበው ለምንድነው ሰው በተፈጥሮ ላገኘው ነገር ሚሞገሰው ወይ ደግሞ የሚናቀው? እኔ በተፈጥሮ በተሰጠኝ አቋሜ ምክንየት ይቀለድብኛል , በቃ እኔን እንደ ሙሉ ሰው የማያዩም ነበሩ
እና አለም ላይ ከዝህ የባሰ ሁኔታ አለ ብለህ ታስባለህ?
ምን ለወጠኝ?
የሆነ ግዜ ላይ በቃ ተስፋ ቆርጨ ግን መፍትሔ ልኖር ይችላል ብየ ማሰብ ጀመርኩ እናም አንድ ቀን ፑል ቤት ውስጥ ፑል እየተጫወትኩ እያለ ድንገት ሳላስብ የሆነ ሰውየን ነጭ ጫማ ረገጥኩት ከዛን ሰውየው እንድህ ነበር ያለኝ ' ቆሻሻ ! ማትረባ ! አስቀያሚ ! አንተ ለምንድነው ምትኖረው? በቃ አሁንም ድረስ ሁኔታውን አስታውሳለሁ አብዛኛው ሰው ሳቀብኝ በቃ በህይወተ እንደዛ መራራ ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም መንገድ ላይ እያለቀስኩ ወደ ቤት ገባሁ ከዛን ልክ ወደ መኝታ ክፍለ ስገባ መጀመርያ ያየውት መፀሀፍ ቅድስ ነበር ... ከዛን በልቤ እንድህ አልኩ አምላክ ሆይ እባክህን ልረዳኝ የሚችል ነገር ተናገረኝ አልኩ ከዛን መፀሀፍ ቅድሱን በግምት ቦታ ከፈትኩት ከዛን መጀመሪያ እንድህ ነበር የሚለው እየሱስም ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ... ሄዴ አንደዛ አይነት ነገር ብሎ ነበር የጀመረው ከዛን እኔ መልዐክት የለውም ብየ ተስፋ መቁረጥ ጀመርኩ ግን ወደ ፈት ያለው ክፍል መልክት ይኖረዋል ብየ ቀጠልኩበት ከዛን እየሱስ አይነ ስውሩን ሰው የፈወሰው ቦታ ደረሰ ከዛን እንድህ የሚል ቃል አነበብኩ ደቀመዛሙርቱ እየሱስን ይሄ ሰው አይነስውር ይሆን ዘንድ ማነው ሀጥያት የሰራው? አሉት,
እሱም እንድህ ስል መለሰ ማንም ሀጥያት አልሰራም እንድህ የሆነው እግዚአብሔር ክብሩን በርሱ ለመግለጥ ስለ ፈለገ ነው አለ በቃ ከዛን እፎይታ ተሰማኝ አዎ ቅድም ሰውየው የተናገረኝ ልብ የሚሰብር መርዛማ ቃል ነበር ሁኔታውን ለመርሳት ከባድ ነበር ይሄ ግን ይለያል በቃ በመጨረሻም ዋጋዬን ያገኘው መሰለኝ ግን በዝህ አላቆምኩም ለሎች ክፍሎችን በዛውም ማንበብ ጀመርኩ ከዛን ቀን ወዲህ እንድህ እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ
" እኔ በሰው መመዘኛ አስቀያሚ ነኝ ዋናው ግን እዝህ ምድር ላይ ለምን ኖራለው? ምኖረው እንደኔ አይነት ችግር ውስጥ ላሉ ማነቃቂያ ለመሆን ከዝህ ምድር የሚበልጥ ትልቅ የሚስራችን ለመናገር ነው" ብየ እያስብኩ መደሰት ጀመርኩ
ከዛ ውጭ የተላያዪ ምስክርኔቶችን ሰምቻለሁ በቃ ህይወትን ማጣጣም ጀመርኩ ስለ አላማየ ማሰብ ጀመርኩ ግን እንደዛም ሆኖ በአቋሜ ሚቀልድ ነበሩ
ሊቀጥልልህ አሁን ስላለሁበት ሁኔታ ምናምን?
Jun 15, 2023