#relationship የምትወደኝ ልጅ አለች በጣም ነው ምትወደኝ እንደምትወደኝ ስትነግረኝ ዝም አልኳት በጣም ትቀርበኛለች እኔ ግን እንደዛ አላስባትም ነበር የማስቀይማት መስሎኝ በሰአቱ ዝም ማለቴ ይባስ ልጅቷ ጦፈች በጣም ፀፀት እየተሰማኝ ነው ይባስ ብሎ የሆነ ሰአት ስትነዘንዘኝ እኔም ውድድ አደርግሻለሁ አልኋት ተ'ያ በኋላ እኔንጃ ልጅቷ ሁኔታዋ እራስዋን ምታጠፋ ነው ሚመስለኝ አሁን ሁን ከባድ ሆኗል ይሉኝታ ይኸው ሊገለኝ ነው እሷ ባየችኝ ድምፄን በሰማች ቁጥር ትፈነድቃለች እኔ ደሞ ትጎዳለች በሚል ፍራቻና ጭንቀት ውስጥ ገብቻለሁ ሳልፈልገው ሰበብ ምክንያት እያበዛው ውሸታም ሆኛለሁ። ልቤ መጀመሪያ የወደድኳት ልጅ ጋር ነው ያለው መሰለኝ ትንሽዬ ፍቅር እንኳን ለዚች ለየኝም እራሴንም አስገደድኩ አልቻልኩም መጀመሪያ በህይወቴ ያፈቀርኳት ልጅ ይኸው 4አመት እንደማፈቅራት አታውቆም ከሷጋርማ ፍቅር ሳይሆን መጋኛ ነው የያዘኝ መሰለኝ😑 እና ቤተሰቦች በጭንቀት አለኩኝ ኧረ ምን ላድርግ የማልፈልገውን ክፉ ሰው ሆኛለው እንዴት ብዬ ልንገራት አልወድሽም እኮ ካልኋት ትጎዳለች በኔ ምክንያት ደሞ ሰው እንዲጎዳ አልፈልግም ኧረ ምን ልሁን መላበሉኝ😑😥
Jun 01, 2023በአንተ ምክንያት እንዳትጎዳ ከፈለክ ሁሉንም እውነቱን ንገራት አትሟዘዝ
Jun 02, 2023