ሰላም በጣም የምወዳት ፍቅረኛ አለችኝ ግን የተለያየ ሀይማኖት ነን በፍቅር አመት ከ2ወር አልፎናል እና እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ እሱዋ ግን አሁን ላይ ስለ ሀይማኖት ስናወራ ደስ አይላትም ገና የጊቢ ተማሪ ነኝ እና ጊዜው ሲደርስ ትለኛለች በዛላይ የተለያየ ሀገር ነን አምናታለው ግን እስከመቸ እርግጠኛ ልሁን የኔ እምነት መቀየር እንኩዋን ሊሆን የሚታሰብ አይደለም ይኸንን እሱዋም ታውቃለች ግን እኔን ማጣት አትፈልግም እና ምን ይሻላል ግራ ያጋባል ለወሬም አይመችም እስኪ ሀሳባችሁን ንገሩኝ🙏🙏🙏🙏
May 30, 2023ገና 2 ወር ላይ ሆነህ እንዲህ መጨነቅህ ትንሽ ይከብዳል early stage ላይ ናችሁና ፤ ግን ደሞ ምንም ሀይማኖት ላይ ብትሆን እሷ ብድግ ብለህ ሀይማኖትሽን ቀይሪ ያንቺ ልክ አደለም ምናምን እንዳትላት Don't rush to the core point cause its sensitive issue ነውና ፤ ቀስ በቀስ ከዘፍጥረት ጀምሮ ታሪኮችን ከመፅሐፍ ቅዱስ እያነሳህ አጫውታት ፤ ስለ ክርስቲያኖች መለያየት ኦርቶዶክስ ልክ ነች ስንል ከምን ከምን አንፃር እንደሆነ ምናምን ንገራት still ግን ያንቺ ልክ አደለም እንዳትል ያስከፋታልና ግን በራሷ እንዴ ብላ እንድትጠይቅ የሚያደርጋትን ነጥቦች አንሳላት ትንሽ ጊዜ ሰጥተህ የራስህንም ሀይማኖት መሰረታዊ ነገሮችን አጥና የእሷንም ማወቅ ደሞ advantage ይሰጥሃል እርሷንም ወደትክክለኛው መንገድ ለመመለስ ይቀልሃል
May 31, 2023