ሰላም ሰዎች አንድ ግር ያለኝን ነገር አካፍያችሁ መልሳችሁን በትክክለኛው መንገድ እንድትነግሩኝ እፈልጋለሁኝ መፅሐፍ ቅዱስ በብሉይ ኪዳን ላይ እንደሚለው ወንድ ልጅ ፀጉሩን ያሳጥር ሴት ልጅ ደግሞ ትሸፈን አልያም ትላጭ ይላል እና አሁን ላይ ሰዎች ያንን ሲተገብሩት አይታይም ሴትም ፀጉሯን ትገልጣለች ወንድ ልጆችም ፀጉራችንን እናሳድጋለን ለምን ሲባል ብዙዎች የሚሰጡት መልስ ያ ህግ ብሉይ ኪዳን ላይ የነበረ ነው ስለዚህ ያ ህግ አሁን ላይ አይሰራም ይላሉ ነገርግን የእግዚአብሔር ቃል ዘመን የማይሽረው ነው ስለዚህ የቱ ነው ትክክል አሁንም በዛ ህግ መመራት አለብን ወይንስ አሁን የምናደርገውን መቀጠል አለብን ??
May 29, 2023ሀዲስ ኪዳን ላይ እኮ እንዲህ ይላል “ወንድ ጠጉሩን ቢያስረዝም ነውር እንዲሆንበት፥ ሴት ግን ጠጉርዋን ብታስረዝም ክብር እንዲሆንላት ተፈጥሮ እንኳ አያስተምራችሁምን? ጠጉርዋ መጎናጸፊያ ሊሆን ተሰጥቶአታልና።” — 1ኛ ቆሮንቶስ 11፥14-15
May 30, 2023