ወግዳይት milew music lay mejemeriya felkesh yetegegnesh mnamn milewn dro tmrtbet enzemrew neber ena yesu mulu gtm yalew pls lakulgn
May 28, 2023ወግዳይት ዘፋኙ ነው። ዘፈኑ ደግሞ ጥሩ ሙዚቃ። ""ሙዚቃ በክቡር ዶ/ር ከበደ ሚካኤል ፈልቀሽ የተገኘሽ ከሹበርት ራስ ከቤቶሸን ናላ ከሞዛርት መንፈስ ከሾፐን ትካዜ ከያሬድ ልቡና መዓዛ የሞላብሽ የብስጭት ቃና ረቂቋ ድምፅ ሆይ ውቢቷ ሙዚቃ ንጹሕ እንደ ጸሐይ ውብ እንደ ጨረቃ የጨዋታሽ ለዛ የድምጽሽ ፍሥሃ የመንፈስ አረቄ የነፍስ እህል ውኃ አገርሽ ገነት ነው ሰፈርሽም ኤድን በስማንሽ ቁጥር ባሳብ መንገድ ሄደን ታጫውቺናለሽ በህሊና ቋንቋ ነፍሴ ካንቺ ጋራ በመተዋወቋ ትሽቆጠቆጣለች ድምጽሽን ስትሰማ ጠባይሽ ሲገለጥ በምድራዊ ዜማ ከገነት መንጭቶ ከሰማይ የመጣ ጣዕሙ አይጠገብም ቢጠጣ ቢጠጣ የትካዜ ከርቤ የብስጭት ዕጣን የመልአኮች ቋንቋ የሱራፌል ልሳን። ታናሽ ነፋስ ሆኖ ድምፅሽ ሰረገላ ውሰጃት እባክሽ ነፍሴን ወደ ሌላ ምግባርሽ አይገጥምም ከዚህ ዓለም ነገር ምንጩን ማን ያውቀዋል ሩቅ ነው ያንቺ አገር:: ባሕሪሽን እንዲያውቀው የሰው ልጅ አእምሮ መመርመር አለበት የነፍስን ተፈጥሮ ነፍስና ሙዚቃ ተመሳሳይ መንታ ባሕሪያቸው ረቂቅ የምሥጢር ሁኔታ ቢሹት ያልተገኘ የመጡት ቦታ ያምላክ ጠባይ ናችሁ ሰማያዊ ጸጋ ምናችሁም አይደል ይህ ምድራዊ ሥጋ ግዞት ነው ሰንሰለት ለናንተ ሥጋችሁ የምትቀጡበት ጥፋት አጥፍታችሁ:: እግዜር የራራ ዕለት ፈጣሪ ጌታችሁ ሥጋ ከሚባለው ከዚህ መጥፎ ጭቃ ይለያያችኋል ቅጣቱን ሲል በቃ። ለእናንተ ግዞት ነው የዚህ ዓለም እድሜ ሞት ግን ይቅርታ ነው የሕይወት ፍጻሜ የተፈረደበት ዋና ጥፋተኛ ነፍስ ነች ባለዕዳ መሬት እስረኛ ሙዚቃ እህቷ ነች በመንፈሷ ቃና የተከተለቻት ልቧን ልታጥናና ከሰማይ ተነስተሽ እመሬት ድረስ ዘላለም ያለሽው በመመላለስ ድምፅሽ የሚያጽናናን ተልእኮ ወደ እኛ አንዴነሽ ሙዚቃ የንፍሴ ጓደኛ:: በመሄድ በመምጣት ምድርን ሰትጓበኚ ሰውን ከእግዚአብሔር ጋር የምታገናኚ::""
May 29, 2023