እሽ አንድ ነገር እንድትረዱኝ ፈልጌ ነበር ምን መሰላችሁ የ 12 ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ እና እስካሁን ለ Entrance ፈተና አልተዘጋጀሁም በ ስልኬ ምክንያት ማለት ነው ነገ በቃ አነባለሁ እል እና ግን አልተገብረውም የስልክ ሱስ ይዞኛል ከዚህ ሱስ ምን ባረግ ነው ምወጣ? በጣም ተቸግሪያለሁ😔
May 28, 2023በስልክህ ከዩትዩቭ የትምህርት ቪዲዮ የፈተና ጥያቄዎችን በቪዲዮ ፈልገህ ትንሽ እይ ብራዘር እኔ አምና አይሆኑ አወዳደቅ ነው የወደኩት ስላላጠናው ብሬ ሰራልን አልልም ዩቩ ገብቼ ኮርጃለሁ ብለህ እንዳታስበው ካለፈ በኋላ ነው የሚቆጭህ እኔ ውጤት ወጥቶ ጀለሶች ዩቪ ገብተው እኔ ሰፈር ስቀር የገባሁበት ድብርት አሁንም አለቀቀኝም እንዳይቆጭህ ትንሽ ሞክር😒
May 29, 2023