ሰላም ቤተቦች 🙏 በፈጣሪ እንዳታልፉት የሆነ ነገር ጻፉልኝ?... ፍቅረኛዬ ከወንድሟ ጋር ነው የምትኖረውና... እና የገዛ የወንድሟ ጓደኞች እቤት ድረስ እሱን ብለው የመጡ መስለው በጣም ያስጨንቋታል ያስቸግሯታል ! እሱ በማይኖርበት ሰአት እየመጡ በጣም ያስቸግሯታል .. እሷ እኔ ጋር መጥታ ስቅስቅ ብላ ከማልቀስ ውጪ ሌላ ምንም አታደርግም ..ለወንድሟ ልትነግረው ብትሞክርም እሱ ከምንም አልቆጠረውም .. በጣም ጭንቀት ውስጥ ገባች ጭራሽ ይጥላት ጀመር ጥሩቀን ይመጣል ብዬ ብታገስ ሰሞኑንማ እቤት ድረስ ሰክሮ ጓደኞቹን እያመጣ ማሳደር ጀምሯል .. ደውዬ ለወንድምሽ ልንገረው ስላት ለሚገባው ነው መንገር ጭራሽ ወንድሜኮ እንካ ውሰድና እንደፈለክ አድርጋት ብሎ እኔን ለጓደኛው ሰቶታል ስለዚህ ዋጋ የለውም ትለኛለች .. ለሚያስቸግራት ልጅ ብነግረው ደግሞ ሂዶ ስለኔ ይናገርና ግንኙነታችንን አደጋ ላይ ይጥለዋል ... ምን ላድርግ ?? በማርያም አንድ ነገር በሉኝ ጨንቆኝ ነው😞😢
May 27, 2023ፍቅረኛህ ስታዝን አብረህ አትዘን። የሀዘኗን ገመድ ቆርጠህ ጣለው። ወንድ አይደለህ? ታዲያ ጠብቃት እንጂ
May 28, 2023