የሚንስትሪ ካርድ እና የልደት ካርድ የ ሁለት ዓመት ልዩነት አለው አንዴት ነው ግዴታ ፓስፖርት ለመውጣት የ ሚንስትሪና የልደት ካርድ እድሜ መመሳሰል አለበት ?
May 20, 2023ዋናው የሚኒስትሪ ካርድ ነው። ብዙ ሰው የልደት ካርድ የለውም ፣ ያላቸውም ከአመታት በኋላ ይጠፋል እንደ ትምህርት ማስረጃ በጥንቃቄ ስለማይቀመጥ። ቀበሌ ሂደህ ራስህ በነገርካቸው መሠረት ነው የልደት ቀን ሰርተፊኬት የሚሰጡት። እኔም በቅርቡ ነው የተቀበልኩት። ምንም እንኳን የልደት ሰርተፊኬቴን አባቴ በጥንቃቄ ቢያስቀምጥልኝም ፣ አያስፈልግም አሉኝ ብዙሀኑ ስለሌለው። እናማ ወደድክም ጠላህም ለስራ ቅጥር የሚንስትሪ ካርድ ላይ ያለው እድሜ ነው የሚቆጠረው ፣ በሱ መሠረትም ነው ጡረታ የምትወጣው። ምናልባት ሰምተህ ከሆነ አንዳንድ ሰዎች በልጅነት ቶሎ ስራ ለመቀጠር ብለው እድሜያቸውን ጨምረው ሞልተው ፣ በመጨረሻ ትክክለኛው እድሜያቸው ሳይደርስ በጡረታ ይገለላሉ። ውጭ ሀገር ሂዶ የመስራት እቅድ ካለህ ደሞ ፓስፖርትህም ስለሚታይ ከሚኒስትሪው እድሜ ጋር አመሳስለው። እናማ የሚንስትሪ ካርድህን እድሜ ተቀበለው!
May 21, 2023