Selam sewoch beteseboche endageba yfelgalu nikam asrewal 1amet tebqognal gn ene magbat alfelgm 1 amet sitebk andm ken slk alanesahuletm ahun endemayhon asregche snegrachew besu hiwet techawetsh alugn mn yshalal lesu SL ena lebeteseboche SL malfelgewn sew lagba weys enbi lbel
May 15, 2023እንደ ሸሪዓው ከሄድን ያላንቺ ፈቃድ መዳራቸው ስህተት ነው። ይህን የማድረግም መብት የላቸውም። ትዳሩ ውስጥ የምትኖሪው አንቺ እንጂ እነርሱ አይደሉም። እንዲህ አይነት ነገር የሚፈጠረው ወላጆቻችን ለዲን ያላቸው እውቀት የወረደ ሲሆን ነው። ማወቅ ያለብሽ እነርሱ ያልወደዱልሽን ወንድ ማግባት እንደማትችዪም ጭምር ነው። There are some exceptions though.. በድብቅ በሐራም መንገድ እየተጓዝሽ እንደሆነ ከደረሱብሽ አንቺ በሐራም ከምትወድቂ አንቺን የመዳር መብት አላቸው። ምክንያቱም ባንቺ የተነሳ አላህ ፊት መጠየቅ ስለሌለባቸው። ቢቻል ይህንንም አስመርጠውሽ ቢሆን የተሻለ ነው። ሲቀጥል አንቺን ልመክርሽ የምፈልገው.. ይህ ዘመንና ፊልም አመጣሽ ፍቅር አስበሽ ከሆነ ማግባት የማትፈልጊው አስገድደው ቢድሩሽም የሚፈርድባቸው አይኖርም። ለትዳር የመጣልሽ ሰው የአላህን ሐቅ የማይጠብቅ፣ የማይሰግድ፣ የማይጾም፣ ወላጆቹን የማያከብር፣ ሱሰኛ ከሆነ ሙሉ በሙሉ ኒካሑን ውድቅ ማድረግ ትችያለሽ። ከዛ ውጭ ስላየሽው ብቻ 'አልወደድኩትም' ብለሽ ወይም 'ሌላ የወንድ ጓደኛ አለኝ' ብለሽ እርሱን መግፋትሽ ጥሩ ነው የሚል አመለካከት ያላቸውን ሸይኾች አላየሁም። በግሌም አላምንበትም። እንዲህ አይነት ችግርም ሲገጥምሽ እዚህ በእውቀት ያልዳበርን ሰዎችን ሳይሆን ማማከር ረሱል (ሰ ዐ ወ) እንደመከሩን ሰለተል ኢስቲኻራ ሰግደሽ ጥሩ የአላህ ባሮችን ማማከር ነው ያለብሽ። ለሌላ ጊዜ ትምህርት ይሁንሽ። በተረፈ እኔ ካንቺ ፍላጎት ጎን ብሰለፍም ወንድማዊ ምክሬ ይህን ትዳር ባትገፊው ምክሬ ነው። አስፈላጊ ከሆነና መተባበር የምችለው ነገር ካለ በዚሁ አናግሪኝ።
May 15, 2023