ሰላም። የዘንድሮ ማትሪክ ተፈታኝ ነኝ። እባካችሁ ማትሪክ ሊደርስ ሲል የሚፀለይ ፀሎት ካላችሁ ላኩልኝ። እንዲህ አይነት ፈተና በጥናት ብቻ አይታለፍም።
May 11, 2023+ ተማሪዎች ፈተና ከመፈተናቸው በፊት ይህን ይጸልዩ + ቅዱስ ቄርሎስ ሣድሳዊ ዘእስክንድርያ የደረሱት +++ ጸሎት +++ ‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ! አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡ ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡ ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንድትረዳኝ እለምንሃለሁ፡ ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡ ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!" ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ጥቅምት 2014 ዓ.ም. ለዚህ ሰሞን ተፈታኞች ፈጣሪ መረጋጋትን ይሥጣችሁ::
May 12, 2023