Hii guys!!! voluntary (በጎ አድራጎት) የምታውቁት ካለ ጠቁሙኝ ባለኝ ጉልበት እና ጊዜ ለመሳተፍ ፈልጌ ነው። ለምሳሌ:- እንደ "ሙዳይ" ምናምን ያለ ተቋም ግን ቅርብ ጊዜ የጀመረ ተቋም ቢሆን ደስ ይለኛል ከ3-4 ዓመት ያስቆጠረ። እድሜ: 23 በወር 12 ቀን ስራ ላይ ነኝ እሁድን ሳይጨምር ሌላውን ቀናት እረፍት። አድራሻ: አ.አ #ስለ በጎ ትብብራችሁ አመሠግናለሁ ✊
May 05, 2023እንደአንተ አይነቱን ያብዛልን በቅድሚያ... በመቀጠል ስፔሲፊክ ቦታዎችን ለግዜው አላውቅም ግን ለምሳሌ እነጌርጌሶን ሜቄዶኒያ ኒያና እና የመሳሰሉት አረጋዊያን እና የአእምሮ እክል የገጠማቸው NGOዎች ጋር ጎራ ብትል በማንኛውም ሰአትና ግዜ በአቅምህ ማገልገል ትችላለህ ብዙዎችም ያንን ያደርጋሉ ኢቭን ቁጭ ብሎ እነዚህን ሰዎች አለሁላችሁ እያሉ ማውራት ማጫወት በራሱ ትልቅ እረፍት ነው ከገንዘብም በላይ ስለዚህ የሚቀርብህ ቦታ ብትሄድ ባለቤቶቹ በደስታ ነው ሚቀበሉህ... በተጨማሪም ትራፊክ ማስከበር ላይ ሰው እና መኪናን ማስተናበር አንድ ዘርፍ ነው በበጎ ፈቃድ የሚሰሩ ስለዚህ ጥቂት ብትጥር ሀሳብህን ሚያሳኩልህ ቦታዎች አታጣም ... በተጨማሪ የረሳሁት (ሐመረ-ብርሀን የተሰኘ ብርሀናን የሚደጉሱ ወጣቶች የተሰባሰቡበት አሮጌው ፖስታቤት ጏሮ አሉ በቅርቡ እንደውም ጥሩ ኤግዚቢሽን አዘጋጅተው ነበር ለበለጠ መረጃ ቲክቶክ ላይ (ሐመረ ብረሀን ብለህ ብትፈልግ ሙሉ መረጃ ታገኛለህ እዛም የአቅምህን መርዳት የምትችልበት ብሎም ለሀገር የሚጠቅም እውቀትን ምትሸምትበት ይሆናል ብዬ አምናለው ጎራ ብለህ ብትቀላቀላቸው)
May 06, 2023