Selam beteseboche Eje lay 2million birr ale Hasabe demo Usa or canada mehed nber yefelkut so endet nw behgawi menged le sra mehed yemchlw ? Birre fail sayaderg malte nw
May 02, 2023በውስጥ አውራኝ እያሉ የሚወተውቱህን ተወት አድርገህ አንድ ነገር አስብ። "ከሐገር ወጥቶ መስራቱ ሐገር ውስጥ ከመስራት ይሻላል" ብለህ አለማሰብን አስብ። በ200k እና ከዚያ በታች ባለ 'ካፒታል' እየተነሱ ወዳሰቡት የደረሱ እያሉ 2M ብር ይዘህ ገንዘቡን ከሐገር መውጫ አድርገህ ማሰብህ ስህተት ነው። ከቤትህ ወጣ ስትል በየቦታው የምታየው ነገር ሁሉ የስራ መስክ ነው። ባይሆን አንድ ነገር ልጠቁምህ.. ወደ ክልል እና ዞን ከተሞች ወጣ ብለህ በህጋዊ መንገድ መሬት ግዛ። ትንሽ ቆየት ብለህ ሽጠው። በትንሹ ጊዜው ዛሬ ገዝተህ ነገ መሸጥ ሲሆን እጅግ በጣም ትንሹ ትርፉ 50,000 እና ከዚያ በላይ ነው። በዚህ መልኩ ዘለግ ላለ ጊዜ እየሰራኀው ከጠነከርክ ወዲህ ስራህን ታሳድገውና መሬት ገዝተህ ቤት ሰርተህበት ወደ መሸጥ ታድጋለህ። ከዚህ በኋላ የሚይዝህ ነገር አይኖርም። ሀብት ከመጣልህ ወዲህ ገንዘብህን ባንክ አታስቀምጥ። ኢትዮጵያ ውስጥ ገንዘብን በባንክ ማስቀመጥ ገንዘብን መግደል ስለሆነ መሬት ገዝተህ አስቀምጥበት። አንተ ተኝተህ መሬትህ "ጊዜ" በሚባል መሳሪያ ራሱን ያፈረጥማል። እነዚህ ስራዎች አያምልጡህ። ሌላ ስራ ከፈለግክ እጠቁምሃለሁ።
May 04, 2023