ሰዎች እንዴት ናችሁ ጥያቄዬ ይቺ አለም ፍትሀዊ አይደለችም አባቴ በጣም ይሰራል በጣም ለበአል እንኳን ቤት አይቀመጥም ግን በቃ ወፍ ለቀን ሆድ ነው እንጂ ተቀማጭ የለ ይሄንንም እያየ ግን ዝምብሎ ይሰራል ግን በውስጡ ቆስሏል 😭 እና ደሞ ጎረቤቶቻችንን ሳይ ምንም አይደክሙም ቁጭ ብለው ነው በቃ የሚያገኙት ዘና ያለ ህይወት ይኖራሉ ግን የኛን ሳይ እንደዛ እየለፋ ለምን እንደማይቀመጥ ነው ችግሩ ምን ይመስላችኋል አባቴ እያሳዘነኝ ነው በጣም
Apr 29, 2023አንዳንዴ ህይወት እንዲህ ናት። ነገር ግን በጎረቤቶችህ የምትቀና ከሆነ ይሄን ሃሳብህን ማቆም ይኖርብሃል። በዚ ጉዳይ ብዙ ምክንያቶች ሊነሱ ይችላሉ። 1ኛው የሥራ መደብ ነው፦ የአባትህ position እና የነሱ position የሚለያይ ከሆነ ይህ ይፈጠራል 2ኛ የቤተሰብ ቁጥር ነው 3ኛ ገንዘብ አጠቃቀም ነው፦ አንዳንድ ቤተሰቦች ገንዘብ አጠቃቀማቸውን የደላ ህይወት የሚኖሩ የሚያስመስላቸው አሉ። ከሁሉም በላይ ግን ትልቁ ትጋትን እና ጊዜ በአንድ ላይ የማጣመር ጉዳይ ነው። ‟መስራት ባለብኝ ጊዜ አርፌ፤ ማረፍ ባለብኝ ሰራው” -ትላለች እናቴ። In real world, በጉብዝና በወጣትነት ጊዜያቸው መታተር ባለባቸው መንገድ የሰሩት ብዙ ዋጋ አስቀድመው የከፈሉ ሰዎች አብዛኞቻቸው ትልቅ ቦታ የደረሱ ናቸው፥ የቤተሰባቸው ህይወትም የተቃና እና ወጣ-ውረዱ የማይከብድበት ነው። ነገር ግን በወጣትነት እድሜያቸው አቋራጭ መንገድ እየተጠቀሙ የነበሩት ሰዎች ጊዜው ሲያልፍባቸው ከወለዱ ከከበሩ በኋላ ከህይወት ጋር ይታገላሉ። እናም ይህ የብዙ ቤተሰብ ታሪክ ታሪክ ሆኖአል።
Apr 29, 2023