ማርያም በጣም ብዙ ትርጉም ነው ያለው 1) በአርያም ያለ ማር (ምግብ)። እንዴት? ቢሉ እንደ ምድር ምግብ የሚበላሽ የሚበሰብስ በልተውት ድጋሚ የሚያስርብ ሳይሆን አንዴ በልተውት ሁሌ የሚያረካ የመላዕክት ምግብ ማለት ነው። መላዕክትስ ምግባቸው ምንድነው ቢሉ ምስጋናቸው እንደሆነ እንረዳለን። እንዲሁም የክርስቶስን ስራ እና ጥበብ ለተረዳ እሱ አስገኝቷት እሱን ያስገኘችልን ድንቅ እመቤት ማርያም ብቻ ናት። እኔ ኃጢአተኛው እና ደካማው ልጇ ልጠራት ባይገባኝም እናቴ ናትና እንድጠርት እና እንዳመሰግናት የወደደች የዓለም ንግስት ነች።
Apr 29, 2023