የኢትዮጵያ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የልዩ ተሰጥኦ ልማት ኢንስቲትዩት በዚህ አመት ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር ይጀምራል፡፡ ==================== ተቋሙ በሀገራችን በተለያዩ አከባቢዎች የሚገኙት ልዩ ተሰጥኦ እና ተውህቦ ያላቸው ተማሪዎች ገብተው የሚማሩበት ኢንስቲትዩት ነው፡፡ ለተቋሙ የሚሆን የትምህርት ቀረፃ ላይ ግብዓቶችን ለመሰብሰብ ያቀደ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉት ተማሪዎች እንዲሁም ከመደበኛ የትምህርት ስርዓት ውጭ በግል ልዩ ተሰጥኦ ያላቸቸው ተማሪዎች የሚማሩበት ሲሆን በልዩ ስርዓተ ትምህርት፤ ልዩ ዝንባሌና ተሰጥዖቸውን ባገናዘበ ሁኔታ ትምህርት እንዲሰጣቸው የሚደረግበት ተቋም ነው፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ሲሳይ ቶላ ባለ ልዩ ተሰጥኦዎች የመደበኛ ትምህርት መከታተያና መዘዋወሪያ ጊዜን ሳይጠብቁ ወደሚፈለገው ከፍታ እንዲሸጋገሩ የሚያስችል ተቋም ነው ብለዋል፡፡ ተሰጥኦዋቸውን በመደገፍና በማበረታታት ስራዎቻቸው ወደ ማሀበረሰቡ ገብተው ሃብት እንዲያመነጩና የስራ እድል እንዲፈጥሩ በማድረግም የሀገራችን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥን ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ለዩ ተሰጥኦ ልማት ኢንስቲትዩት በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ ብቃት ያላቸው ሳይንቲስቶች፣ ኢኖቬተሮች፣ ቴክኖሎጂስቶች እና አመራሮች ለማፍራት መሰረት የሚጥል ኢንስቲትዩት ነው። ኢንስቲትዩቱ በዚህ አመት የመማር ማስተማር ስራውን የሚጀምር ሲሆን በቀጣይም 1ሺ ተማሪዎችን የመቀበል አቅም አለው። yet new yh school
Oct 02, 2020burayu meselegn
Oct 03, 2020