#የግማሽ_ዓለም_ፍፃሜና_ተመልሶ_መግነን_የሚጀምረው_የኢትዮጵያ_ኃያልነት በእኛ በኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠር አርብ #ሚያዝያ 5፣ 2021 ዓ.ም. ወይም በፈረንጆቹ የዘመን ቀመር #April 13, 2029 ላይ የአስትሮይድ መለያ ስሙ #Apophis የተሰኘ ግዙፍ የድጋይ ቋጥኝ(Asteroid) ምድራችንን እንደሚመታት በትክክል ተረጋግጧል። የቻይና ውስን የምስራቅ ግዛቶች፣ ሙሉ የሰሜን አሜሪካ ግዛቶችና የፓስፊክ ውቅያኖስ በአስትሮይዱ የሚመቱ የምድር አካባቢዎች ናቸው። በዚህ የተነሳም በትንሹ እስከ 2 #ቢሊዮን የሚደርስ የዓለም ህዝብ በአንድ ቀን ሊያልቅ ይችላል። የአውሮፓውያን የጠፈር ምርምር ድርጅት(ESSA) ተመራማሪዎችም በጊዜአዊ መለያው 25931(2014 NY73) ሲሉ የሰየሙት ይህ ግዙፍ የሚነድ የእሳት ቋጥኝ(Meteorite Asteroid) ወደ ምድር ደርሶ ሲላተም በሚፈጠረው ከባድ ፍንዳታ፣ ከግማሽ ቢሊዮን በላይ የሚሆነው የዓለም ህዝብ ለዐይን ስውርነት ሊዳረግ ይችላል ሲሉ ተናግረዋል። አክለውም በሰው ልጅና በእንስሳት ላይ አዲስ የቅርፅ አፈጣጠር(Physiological Structure) ለውጥ፣ አዳዲስ ተላላፊ በሽታዎችና ታይተው የማይታወቁ የማዕድን ግኝቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። ዓመተ ምህረቱ፣ ቀኑ፣ ሰዐቱም ሳይቀር በአባቶቻችን የባህረ አሳብ ቀመር ላይ የተጠቀሰው ይህ ክስተት "ኢትዮጵያን አይመለከትም" በሚል ማሳሰቢያም ቃል በቃል የተገለፀ ነው። የቻይናና የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋማት ለዚህ የማይቀርላቸው አደጋ መፍትሔ የሚያፈላልግ የጥናት ግብረ ኃይል በጋራ አዋቅረው ላይ ታች እያሉ ነው። መቼም ክፉ እጣቸው/መውደቂያቸው ነውና ማንም ትኩረት አድርጎ እንዳይከታተላቸው የምርምር ግብረ ኃይሉን ሂደትና ውጤት ብዙም አይናገሩም። ኢትዮጵያ ኃያላኖች ሲዋረዱ ለማየትና ለመመስከር የተፈጠረች አገር በመሆኗ የሌሎች ስጋት አያሰጋትም፤ አያውካትምም። በተለይ ከሚያዝያ 5፣ 2021 ዓ.ም. በኋላ ኢትዮጵያ የዓለም ህዝቦች ተሰደው ሊኖሩባት የሚጎርፉባት፣ ከመዓትና ቁጣ መጠለያ የሆነች፣ ኢኮኖሚዋ የሚፈረጥም አገር እንደምትሆን አያጠራጥርም። እንዳትጠራጠሩ!! ዐይኖቹን ለቅፅበት በማያነሳባት አገር ኢትዮጵያ ውስጥ የፈጠረን አምላክ ይመስገን!! ይግነን!! አሁንም አምላካችን እግዚአብሔር አገራችንን አብዝቶ ይባርክልን!!
Oct 03, 2020