እድሜያችን ሀያዎቹ መጀመርያ ላይ ነው እንዋደድም ነበር ... እርሷ ግን ኩላሊቷን በጣም ያማታል መታከም አለባት እኔ ደግሞ ወጭዋን መሸፈን አልችልም ... አባቷ ከ ወዳጃቸው ጋር ተነጋግረው አሜሪካ ለልጁ ሊድሩለት ነው እናም ሊያሳክማት ... በዚህ ሁኔታ መለያየታችን ግድ ሆነ ምን እንደማደርግ አላውቅም ባዶ የሆንኩ ያክል የማዋየውም ሠው አላገኘውም
Apr 16, 2023ሀቢቢ ፈጣሪ ይማራት🙏 አንዳንዴ ላይፍ ታስገድድሀለች ከሁለት መጥፎዎች አንዱን መምረጥ ነው ፍቅርህን አጥተህ በህይወት ከምትኖርልህ እና ፍቅርህን ሳትለቅ እስክትሞት መጠበቅ በጣም ከባድ ነገር ነው ይገባኛል ግን ፈጣሪ እንዲረዳህ ፀልይ እስኪ እኔም በፀሎት ከጎንህ ነኝ🙏
Apr 17, 2023