አረ ቤተሰብ እስቲ ጨንቆኝ ነዉ 1 አመት የ electrical ተማሪ ነኝ ቤተሰብ ደሀ ኘዉ fATHER ለኛ ብቻዉን ይለፋል ማዘር ደሞ ስራ የላትም እና ቤት ውስጥ 5 ነን ግን ከ father ውጭ ማንም ስራ ያለዉ የለም እና አሁን እሱም ደክሞታል በአል እራሱ አኔ ብዙም ማውረት አልፈልግም ግን life ጨነቀኝ ሰዉ ሁሌ ሲስቅ ሲጫወት ነዉ የማይ እኔ ግን ጓደኞ የለኝ ስራ የለኝ ቀኑን ሙሉ ተጨንቄ ነው የምዉል ሰዉነቴም ከሳሳ እስት አንደት ነዉ ቆይ የሆነ ነገር በሉኝ
Apr 15, 2023አይዞህ ወንድም አለም ሁሉም ያልፋል ሲባል ቃሉን መናገር ቀላል ሊመስል ይችላል ግን እውነታው እንደዛ ነው ... ሁሉም ነገር በምድር ላይ ያለ አላፊ ጠፊ ግዚያዊ ነው ... ሁላችንም ባለን ነገር ላይ ተጠቅመን ፈጣሪን እያመሰገንን እና እየፀለይን መንገዳችንን ቀና እንዲያደርግልን መጣር መጠንከር ነው... ለምሳሌ አንተ ብሩህ ጭንቅላት አለህ ስለዚህ ለምን ባለህ ትርፍ ግዜ ከክላስ በኃላ የተወሰኑ ልጆችን ፈላልገህ ማስጠናት አትጀምርም ብዙዎች ያንን እያደረጉ ቤተሰቦቻቸውንም እራሳቸውንም ይደጉማሉ... ካንተ በታች ያሉትንም አቅም የፈቀደውን ስራ እንዲሞካክሩ አግዛቸው ብርታትም ትሆናቸዋለህ... ብቻ አንተ ያለህበትን ህይወት ማማረር ለግዜው ገታ አድርግና ምን አለኝ ብለህራስህን ተመልከት (ጭንቅላት አለህ/ሙሉ ጤነኛ ነህ ስገምት/ ትራመዳለህ / ታያለህ....) እነዚህ ነገሮች ሲኖሩን ቀላል ይመስላሉ የሌላቸውን ግን ስናስተውል ማመስገን እና ባለን መደሰት መጣር እንጀምራለን.. ስለዚህ ቢያንስ በአሉን ባላችሁ ነገር ተደስታችሁ እለፉ ወንድሜ(ኖሮኝ ባደርግልህ ደስ ይለኝ ነበር ግን ለግዜው እኔም እጅ አጥሮኛል ቢሆንም ግን አንተ ከልኩ በላይ አትጨነቅ (አንዳንዴ ህይወትን ከመፋለም ይልቅ አብሮ ሰርፍ በማድረግ የምትፈልገው ቦታ መድረስ ትችላለህ ስለዚህ በርታ ወንድም አለም መልካም የብርሀነ ትንሳኤ በአል ከነመላው ጤናማው ቤተሰብህ ይሁንልህ ወንድሜ🙏🏾
Apr 16, 2023