Selam sewoch hulum ngr dekemegn menor erasu astelagn mn larg yemr fetari erasu zim yalegn tetelagn yahil tesemagn koy fetari lijun yitelal ende e
Apr 12, 2023ክርስትያን ከሆንሽ እየጠየቅሽ ያለሽው ላንቺ ብሎ የሞተው ኢየሱስ ክርስቶስ ጠላኝ ብሎ እንደማሰብ ነው። ስለሽዋል ላንቺ ብሎ እስከሞት የደረሰው ሲጠላሸ ከዛ በላይ ደግሞ ሊሞትልሽ የሚገባ ምንም መልካም ምግባር ሳይኖርሽ በደለኛና በእርሱ ላይ እያመፅሽ እርሱ ሞተልሽ! እንደ ምክር ግን ማማረር ነው የያዝሽው ማማረር ደግሞ አጥያት ነው መጽሐፍ ደግሞ ምኞት ፀንሳ አጥያትን ትወልዳለሽ አጥያት አድጋ ሞትን ይላል። ስለዚህ የአጥያታችን መነሻ ምኞት ስለሆነ ምኞትሽን መግታት እና ባለሽ ነገር ሁሉ ለማመስገን መትጋት ያስፈልጋል። መጽሐፍ እንዲህ ይላል “ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ መንገዴ ከመንገዳችሁ አሳቤም ከአሳባችሁ ከፍ ያለ ነው።” ኢሳይያስ 55፥9 ስለዚህ የእግዚአብሔር ሃሳብ ከፍ ያለ ነው እንደፈቃዱም ይሰራል አንዳች ግን ከእርሱ ከእግዚአብሔር ብንፈልግ መጽሐፍ ደግሞ እንዲህ ይላል:- መዝሙር 37 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³ በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ። ⁴ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል። ⁵ መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል። ለፀሎትሽም መልስ እግዚአብሔር የዘገየ ቢመስልሽ ጻድቁ ዳዊት በመዝሙሩ እንዲህ ይልሻል:- “ቆይቼ እግዚአብሔር ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኽቴንም ሰማኝ።” መዝሙር 40፥1 ደጅ መጥናት ያስፈልጋል። አጥያታችንን ይቅር እንዲለን በምህረቱም በእርሱ ዘንድ መልካም የሆነውን የልባችንን መሻት ይፈፅምልን ዘንድ! ካንቺ የባሰ አለ፤ እንደ እዮብ ያለ።
Apr 12, 2023