be hmamat gze siseged mibalu negeroch mn mn nachew ena leloch hgoch mtakutn share argugn
Apr 10, 2023Henok: በሰሙነ_ህማማት_የሚፈፀሙ_ስርአቶች:- 👉1 #ስግደት ፦ በስሙነ ህማማት 41 ጊዜ ኪሪያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል ። +++++++++++++++++++++++ 👉2 #ጸሎት ፦በሰሙነ ህማማት በ24 ሰአታት ውስጥ 10 የፀሎት እና የንባብ ሰአታት ይገኛሉ ከነዚህም ከጥዋቱ ✔1ሰአት; ✔3 ሰአት ; ✔6 ሰአት ; ✔9 ሰአት ; ✔11 ሰአት እንዲሁም ✔ከምሽቱ 1ሰአት ; ✔6 ሰአት ; ✔9 ሰአት ✔11ሰአት ; ናቸው ። 👉 በነዚህም ሰአታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊት እና ግብረ ህማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይፀለያሉ ። ++/+++/++++++++++++++++ 👉3 # በሰሙነ ህማማት ;-ብዙ አዝማድ መባልዕት /አዘውትረን የምንመገባቸውን ምግቦች አይበሉም ። ✔ በዚህም ሳምንት እስከ ምሽት 1 ሰአት እንድንፆም ; ✔ይኽውም ቆሎ ዳቦ ዉኃ እና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተፅፎ ይገኛል ። +++/++/+++++++++++++++++ 👉4 #አለመሳሳም ፦ አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩ ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠዉ መሳሳም አይፈቀድም ። #መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ። 3:13 ማቴ 10 :38 ሜቴ 26 :29 ++++++++++++++++++++++++ 👇👇👇 👉 5 #አክፍሎት ፦ እመቤታችን ያቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውሃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳዔው መቆየታቸውን በማሰብ የሚፆም ነው ። +++++++++++++++++++/++/ 👉 6 #ጉልባን ፦ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በፀሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆንትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው ። +++++++++++++++++++++(+ 👇👇👇👇 👉 7 #ጥብጠባ ፦ይህ ምዕምናን በሰሞነ ሕማማት የፈፀሟቸውን ኃጢያቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስቅለት የሚቀበሉበት ነው ።ይህም የጌታ ምሳሌ ነው ። +++++++++++++++++++++++ 👉 8 #ቄጠማ ፦ጌታችን ብርሃነ ትንሳዔውን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የሾህ አክሊል በመድፍቱ ምሳሌም እራሳችን ላይ እናስረዋለን ። +++++++++++++++++++++++ #የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ #መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡ በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ #አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
Apr 10, 2023