ሰላም ኦርቶዶክሳውያን የኔ ጥያቄ ምን መሰላቹ እንደ ሚታወቀው ከነገ ጀምሮ ሰሞነ ህማማት ነው እና በዚህ ሳምንት ሚደረጉና ማይደረጉ ብዙ ነገሮች አሉ።ግን ደሞ አንዳንዴ ሰዎች አይደረግም ሚሉኝ ነገር ምንም ምክኛታዊ አልሆን ይለኛል ለምሣሌ ማማተብ ነጠላ መስቀልያ መልበስ ከዳዊትና ውዳሴ ማርያም ውጪ ሌሎች ፀሎቶችን ማድረስ....ታድያ ይሄ ነገር እውን ስርዓተ ቤ/ክ ነውን? ከሆነ ምክኛቱን ካልሆነ ደግሞ ትክክለኛ ስርዓቶችን ብትነግሩኝ🙏
Apr 08, 2023ልክ ናቸው ወንድሜ ሰሞነ ሕማማት ዘመነ ብሉይ 5500 ዘመን የነበረው የመከራ ጊዜ የሚታሰብበት ነው ይህም ማለት በሌላ አማርኛ ዘመነ ነቢያት ክርስቶስ ገና ይወለዳል ይመጣል እያሉ ትንቢት የተናገሩበት ጊዜ ነው ማማተብ የለም መስቀለኛ ነጠላ መልበስም የለም ለምን ቢሉ በሕማማት ጊዜ ምናስበው መስቀል የቤተ ክርስትያን ትምክህት እና ሰይጣንን ማራቂያ የነበረበትን ሳይሆን የአይሁድ የወንጀለኛ መቅጫ የነበረበትን ጊዜ ነው ለዛም መስቀል አንሳለምም አናማትብም ነጠላም መስቀለኛ አንለብስም ከዳዊት እና ከውዳሴ ማርያም ውጭ ሚደርሱ ፀሎቶች ሚነበቡ መፃህፍት አሉ እነሱም መልክአ ሕማማት ግብረ ሕማማት.. የመሳሰሉት ናቸው ከውዳሴ ማርያምም ማይባሉ ሚዘለሉ አሉ ሌሎች መልክአ መልኮች እና የቅዱሳን ገድላት አይነበቡም ለምን ቢሉ ቅዱሳን የተጋደሉት ስለ ክርስቶስ ነበር ስለ ስሙ ለማዳን ስለ መምጣቱ ሥላ አምላክነቱ... በሰሞነ ሕማማት የነሱ ፀሎት አይደርስም ለምን ቢባል ገና ክርስቶስ ያልተወለደበትን ዘመን ስለምናስብ.... የሳትኩትን ያታመምኩትም ካለ በቀና ልብ እያረማቸሁ አንበቡት እህት ወንድሞቼ🙏🙏🙏
Apr 09, 2023