ምን መሰላቹ ከወራቶች በፊት አንድ ጓደኛ ነበረኝ አሪፍ ላይ ነበርን በመሃል ወሬ ሰምቼ ሳላጣራም ሳልጠይቀዉም ተጣላሁት ወሬዉ ያን ያህል ሚያጣላም አልነበረም በንግግር ሚያልቅ ነበር ግን ቸኩዬ ስህተት ሰራሁ እና አሁን ከልጁ ጋር ድጋሚ ማዉራት ጀምረናል ግን እንደበፊቱ አልሆነም እና የበፊቱን ነገር እንዴት ማምጣት እችላለሁ ስላለበት ሁኔታስ በምን ልወቅ ካላወራሁት አያወራኝም አስፈላጊ ነገር ከሆነ ብቻ ነው ሚያወራኝ እና ምን ላርግ ናፍቆኛል ደሞ እስቲ ምከሩኝ።
Apr 06, 2023በጣም ችኩል ነሽ ልበም ናፍቆኛል ለማለት ራሱ ቸኮልሽ ለማንኛውም ከዚህ ቡኃላ ከውሳኔሽ በፊት ጊዜ ወስደሽ ማሰብ ልመጂ በተረፈ መልካም እድል🤷♂
Apr 07, 2023