please admin aprove ምን መሰላችሁ በጣም በጭንቅ በሀሳብ ነዉ ያለሁት የዩኒቨርስቲው ተማሪ ነኝ እና ፊልዱ አልወደድኩትም እና እቤት ሳልነግራቸዉ መከላከያ ለመግባት እያሰብኩ ነዉ ሌላም ምክንያት አለኝ የኔ የድሀ ቤተሰብ ልጅ ነኝ ጎረቤታችን ደግሞ ሀብታም ናቸዉ እና በድንበር ተጣልተን ሰዉዬ መሬታችንን አልሰጥም ብሎ ክዶ እንደገና ለአባቴ አንተ ተሳድበሀል ተብሎ ሽማግሌዎቹም ለነሱ ፈርደዉ ከብቶች ታርዶበት ብርም ተቀጣ እሺ ብዬ ፈጣሪ ያያል ብዬ ለቤተሰቤ እረፍት በሄድኩበት አስተባብዬ አንዲታረቁ አረኩ አሁን አንደገና እነሱ ልጆቹም ሀብት አላቸዉ እኛን መሳደብ ነዉ የጀመሩት ሰዉ በተሰበሰበበት በዐላት ላይ ጭምር ስም እያነሱ እኛን ድሮ ረዳናቹ እያሉ ከሰዉ ማይጠበቅ ለማዉራት ማይመች ቃላት እየተጠቀሙ እኛን ማሸማቀቅ ጀምረዋል ባለፈዉ አባቴ ሊያሳስሩት ነበር አሁን የመጨረሻ ምርር ነዉ ያለኝ መከላከያ የወጣ ማስታወቂያ አይቼ ነው ልግባ ወይ ወይስ ግራገባኝ በነገራቹ ላይ እዚ ምድር ቆይ ለእውነት ሚቆም ጠፋ ማለት ነዉ ሽማግሌዉም ለብር ሚሰራ በእውነት በጣም ግራ ገብቶኝ እስቲ ሀሳባችዉ አካፍሉኝ
Apr 05, 2023መከላከያ የገባኸው ሀገርህን ለመጠበቅ ነው ወይስ በጎረቤታቸው የተበደሉትን እናት እና አባትህን ተበቅለህ ሀገር የሰጠችህን ኃላፊነትን ለማጒደል? የኔ ወንድም፥ እናት አባትህን መከላከል ከፈለግክ ውጣ እና ሕግ ት/ቤት ገብተህ ጥብቅና ተማር እንጂ የውትድርናን image አታጥፋ።
Apr 06, 2023