ሰላም ለረጅም አመት የቆየ ሱስ ነበረብኝ እና ለማቆም ብዙ ነገር ሞክሬ አልተሳካልኝም ነበረ በመጨረሻም እናቴን በጣም እወዳት ስለነበረ ከአሁን በኃላ ወደዚህ ሱስ ከተመለስኩ እናቴን በሞት ንጠቀኝ ብዩ ለፈጣሪ ማልኩ ግን አሁንም ተመልሼ ወደ ሱሱ ገባሁ እናቴም በ1ወር ውስጥ በጣም ታመመች ከዛ ከ 4 ወር በኃላ አረፈች so አሁን ላይ በጣም ትልቅ ፀፀት ውስጥ ነኝ የእናቴ ሞት ምክንያት የኔ ሱስ እንደሆነ እየተማኝ እራሴን ለማጥፋት እያሰብኩ ነው...so አጋጣሚ ሆኖ ነው ወይስ በእኔ ምክንያት ነው ይሄ ሁሉ መአት የመጣብኝ tell me your opinion i m in a big trouble😭😭😭
Apr 05, 2023ቀላሉ እውነታ ማንም በማንም ህይወት መማል አይችልም ቢምል እንኳን በደሉ በማለው ሰው ነው እንጂ ያኛውማ ምኑን አውቆት። ሌላው የሰው ልጅ አይደለም በመሀላ ራሴን ላጥፋ እንኳን ቢል ቀኑ ካልደረሰ በፍፁም አይሞትም ቀኑ ከደረሰ ግን በአለም ላይ አሉ የተባሉ የህክምና ተቋም ውስጥ እንኳን ሆነው በጉንፋን ይሞታሉ በመጨረሻም ፈጣሪ አንተን ለመቅጣት እንዴት እናትህን ይገድላል non sense አይሆንም ይሄ ሀሳብ? ተረጋጋ እና አሁንም አልረፈደም እናትህ እንድትሆን ምትፈልገውን አይነት ሰው ሆነህ መንፈሷን በማስደሰት ካሳት እንጂ ጭራሽ ብርጭቆ ሰብሮ እንደሚያለቅሰው ልጅ መሆን ተገቢ አይደለም አይዞን ያልፋል ይሄም🙏
Apr 06, 2023