ስጋን የሙስሊም ወይም የክርስትያን ብሎ መከፋፈል ግን ትክክል ነው? ወይስ ቄስ በግ ወይም ሼህ ፍየል አለ ? ወይስ ኃላ ቀር አመለካከት ነው?
Apr 03, 2023ይህ ነገር ከግብጽ ሃገርም የመጣ ባለመሆኑ በቀደምት ክርስትና ያልነበረ መሆኑ እሙን ነው። በአፈ ታሪክ ደረጃ እንደሚባለው ከሆነ ይህ የመጣው ከግራኝ አሕመድ እና ግላውዴዎስ ጥል በኋላ እንደሆነ እና በዛው ትውፊት ሆኖ እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን ይህ ይሁን እንጂ ሳይባረክ ደሞ ሳይፈስ የታረደ እንሰሳ አይበላም። ግን ማሽን በሚያርድበት ዘመን እና ከድሮ ጀምሮ አንዳንዴ በስመአብ ማለት ተረስቶ መታረድን ስናይ የመከፋፈሉ ምክንያት ይህ ሆኖ አይታየኝም። ነገሩ deeply ጥሩ ባክግራውንድ አልነበረውም። Anyways, እንደ ቀላል የጀመረው ቀኖና ሆኖ ስለቀጠለ ከማክበር ውጪ ምንም ማረግ አይቻልም። ካሁን በኋላ ይፈቀድ ቢባል ራሱ ባይፈቀድ የተሻለ ነው፥ በሰባ ምግብ ስም ተጀምሮ በኋላ ሃይማኖትን ከሚያሳጣ፤ ምግቡን ቢከለከል ይሻላል ይላሉ አባቶች።
Apr 03, 2023