ሰላም ቤተሰብ +++ በግል ህይወቴ በደረሰብኝ ክህደት ምክንያት አሁን ላይ ለወንዶች ጥሩ አመለካከት የለኝም ያን ስላቹ በደፈናው ሁሉንም ወንድ እጠላለሁ እያልኩ አይደለም ሶሻል ላይፌ ላይ ከነሱ ጋር ባለኝ ጓደኝነት በጣም ደስተኛ ነኝ በሌላ በኩል ያለውን ፋይል ግን ለጊዜው ዘግቻለሁ ታላቅ እህቴ አግብታለች እና አንዳንድ ጊዜ እሷ ጋር እሄዳለሁ ማለት አድራለሁ አብረን እንጫወታለን ደስ የሚል ጊዜም እናሳልፋለን እኔን ሲያይ ባሏ የሚያሳየው ነገር ግን ጥሩ አይደለም ሰላም ይነሳል የሌለ ሽፍድ ይላል እና እሷ እንዳትነቃ የሚያረገው የማለባበስ ጥረት ያስቀኛል እኔ በማስበው መልኩ ባለጌ እንዳይሆን እየተመኘው እና የሆነ ምልክት ባሳየው ቀጥ ብሎ እንደሚመጣም ጭምር እያወኩ ነው ይሄን ጥያቄ የምጠይቃችሁ የሆነ ተንኮል እያሰብኩ ነው ይሄ ሰውየ እህቷ እንደሆንኩ እያወቀ እኔ ጋር በዚ ልክ አክት ካረገ imagine eski ውጪ ከሌላ ሴት ጋር ሌላ ነገር ላለማረጉ ምን ማረጋገጫ አላት አንድ የምሳሳላት እና የምወዳት እህቴ ናት ማንም ወንድ እንዲጎዳት አልፈልግም በጣም ሲበዛ ታምነዋለች ትወደዋለችም ስለዚህ በምንም ሁኔታ እንደማጠረጥረው ያውቃል እሱ ግን ውሻ ሳይሆን አይቀርም ስለዚህ መፈተን አለበት አይመስላችሁም ይፈተን አይፈተን ምን ታስባላችሁ ?? በተለይ ወንዶች
Apr 01, 2023የፃፍሽበትን መንገድ ሳላደንቅ አላልፍም 🤌🤌🤌 ሲቀጥል ልፈትን ብለሽ ሌላ ታሪክ ውስጥ ገብተሽ ከእህትሽ ጋር እንዳትጣዪ ማድረግ ያለብሽ ለ እህትሽ መንገር ነው ከዛ በጋራ ፈትኑት 🤷♂
Apr 03, 2023