ለ ኦርቶዶክሳውያን ሰዎች ይጠይቃሉ ክርስቶስ ለምን በ ሰው እጅ ሞተ? ከሀጢአት ሊያነፃቸው መቶ ለምን ሐጢያት አስገባቸው? እሱ አምላክ ከሆነ ለምን ጡት ጠባ? ይላሉ ምን እንመልስላቸው ከትህትና ጋር!
Mar 29, 2023ምክኒያቱም ሰው ከኤደን ገነት የተባረረው ባለመታዘዝ ስለሆነ ኢየሱስ ስለእኛ ታዘዘ እስከ መስቀል ሞት ድረስ። “በአንዱ ሰው አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጢአተኞች እንደ ሆኑ፥ እንዲሁ ደግሞ በአንዱ መታዘዝ ብዙዎች ጻድቃን ይሆናሉ።” — ሮሜ 5፥19 ፊልጵስዩስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይሁን። ⁶ እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን መቀማት እንደሚገባ ነገር አልቈጠረውም፥ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፥ ⁸ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፥ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ። ⁹ በዚህ ምክንያት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ልክ ከፍ ከፍ አደረገው፥ ከስምም ሁሉ በላይ ያለውን ስም ሰጠው፤ ¹⁰ ይህም በሰማይና በምድር ከምድርም በታች ያሉት ሁሉ በኢየሱስ ስም ይንበረከኩ ዘንድ፥ ¹¹ መላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደ ሆነ ይመሰክር ዘንድ ነው።
Mar 30, 2023