እኔ አላቅም በቃ እናቴ እኔን ስታረግዝ ልታስወርድ ብዙ ሞክራለች ህክምና ሄዳ ባለቤትሽ ካልፈረመ ምናምን ተባለች ሌሎችንም መንገዶች ሞክራለች ልታስወርደኝ ግን እግዚአብሄር አልፈቀደም ለምን ይመስላችኋል
Mar 28, 2023ለታላቅ ዓሌማ ስለታጨህ ይሆናል ይህችን ምድር እንድትረግጥ የተፈቀደልህ። እንጂማ ባትጠቅም ኖሮ በአባትህ የተሞነጨረ ፊርማ ወይም ጥቂት ኪኒኖችን በመዋጥ ፈጣሪህ እዚያው ያስቀርህ ነበር። ኳስ ተመልካች ባልሆንም.. ክሪስቲያኖ ሮናልዶም ያንተው እጣ ፈንታ እንደነበረው አንብቤያለሁ። ዛሬ ግን በስፖርቱ ዓለም ታሪክ እየሰራ ያለ ሰው ነው። አንተም የተፈጠርክለትን ዓላማ ፈልገህ አግኘው። ደማቅ ታሪክም ስራበት።
Mar 29, 2023