Guys eski tell us kezare 5 ameet befit yasebachut or yakedachut ngr ahun gn lela hiwot eyenorachu kehone i mean ke 5 yr bewala successful ehonalew belachu kaltesakalachu or ketesakalachu / yane tesfa saynorachu hiwot kebduachu ahun gn arif huneta west kalachu becha betmhertm, be seram , be business or money , be marriage lay yane yasebachut ena ahun yehonewn journey akaflun
Mar 26, 2023የመጀመርያ አመት የመቀሌ ሶፍትዌር ተማሪ ነበርኩ። ግን አልተሳካም በጦርነቱ ምክንያት። እኔ ከ ሁለት አመት በፊት በግራፊክስ ቪድዮ ማስተር አደርጋለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን በጦርነቱ ምክንያት ሁሉም ነገር ተዘጋጋ ትግራይ ክልል ውስጥ። ይህም አልተሳካልኝም። ከሁለት አመት በፊት 30K Subscribers ነበሩኝ ዩቲዩብ ላይ ቢያንስ ወደ 300,000 አደርሰዋለሁ ብዬ አስቤ ነበር ፤ የወር ገቢም በዩቲዩብ እስከ 40K እሰራ ነበር 150K የማግኘት እቅድ ነበረኝ። ግን አልሆነም ! በ Adobe After Effects and Premiere Pro Video Editing ጥሩ ስራ እገባ ነበር ብዬ ገምቼ ነበር። ግን እውቀቱ ቢኖረኝም በመንግስቶቻችንና በሀገራችን የአለመግባባት ችግር ሳይሳካ ቀርቷል። ሁለት አመት ትግራይ ስትታመስ ግን እኔ ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ በራሴ ከቤቴ ሆኜ ጨረስኩኝ። አሁን እመቤቴ ትመስገንልኝ አፖችን በመፍጠር Upwork , Envato Market , Amazon, Store ላይ በመስራት እገኛለሁ። ቀጣይ ትልቅ እቅድ አለኝ ! ግራፊክሱን ፣ ዩቲዩብን ፣ ትምህርቴን ፣ ኤዲቲንግ ማሳካት።
Mar 27, 2023