How to develop confidence? በራስ መተማመኔ የወረደ ነው ሰዎችን ቀርቤ መግባባት አልችልም... ሲበዛ የበታችነት ስሜት ይሰማኛል በሰው ፊት ቀና ብዬ መሄድ ራሱ አልችልም ሁልጊዜም በበታችነት ውስጥ ነኝ ገንዘብ ኖረኝ አልኖረኝም brand ለበስኩ አለበስኩም ሁልጊዜ እዛው ላይ ነኝ እና እንዴት ኮንፊደንሴን ማሳደግ እችላለሁ🙏
Mar 26, 2023ብሮ እንደ ብዙ ሰው የበታችነት ስሜት የሚሰማህ ከሆነ ሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት በጣም ምትጥር አይነት ሰው ነህ ማለት ነው ወይም ሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ሆኖ ወይም እንከን አልባ ሆኖ መታየት የምትፈልግ ሰው ነህ ማለት ነው ይህ ባህሪህም ነው ከሰው ያራቀህ፡ ስለዚህ አንድ ማወቅ ያለብህ ነገር ከሌሎች ሰዎች አንተ የተለየህ አይደለህም ሁሉም ሰው አንተ አለኝ ከምትለው ችግር በላይ አለበት ግን ራሱን ተቀብሎ ስለ ሰው ሳይገደው የሚኖር ሰው ከሆነስ እሱ ኮንፊደንት ወይም በራሱ የሚተማመን ነው ማለት ነው። እውነተኛ በራስ መተማመን ሰዎች ይቀበሉኛል ሳይሆን ሰዎች ባይቀበሉኝም እኖራለሁ ምንም አልሆንም፡ማለት ነው፡ ስለዚህ አንድ ልነግርህ ምፈልገው ነግር እውነተኛ ኮንፊደንስ እንዲኖርህ ራስህን ተቀበል egoህን አስወግድ ማለትም ራስ ወዳድነት የሚመስል ግን በድብቅ ስለሌሎች የሚጨነቅ የ አምሮ ክፍል ነው። ስለሌሎች የምትጨነቅ ከሆነ ደግሞ ሀይልህ ባንተ እጅ የለም ማንም ስሜትህ ለይ ሊጫወት ወይ ስሜትህን ከፍ ዝቅ ሊያደርግ ይችላል ራስህን የምትቀበል ከሆነስ ማን አንተ ለይ ስልጣን አለው ? ማንም። ስለዚህ በሰዎች ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ሳይሆን ራስህን መቀበል ባለህ ነገር መኩራት ጀምር. ... ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያቆምህም
Mar 26, 2023