Sewoche eski sela መጠጥ መፅሐፍ ቅዱስ እና የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ምን ይላል eski yemitawku asredunge
Mar 24, 2023መፅሐፍ ቅዱስ ቃል በቃል አትጠጡ አይልም። ግን ለምን መጠጣት እንደሌለብን ምክንያት ይነግረናል:- ምሳሌ 23 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²⁹ ዋይታ ለማን ነው? ኀዘን ለማን ነው? ጠብ ለማን ነው? ጩኸት ለማን ነው? ያለ ምክንያት መቍሰል ለማን ነው? የዓይን ቅላት ለማን ነው? ³⁰ የወይን ጠጅ በመጠጣት ለሚዘገዩ አይደለምን? የተደባለቀ የወይንን ጠጅ ይፈትኑ ዘንድ ለሚከተሉ አይደለምን? ³¹ ወደ ወይን ጠጅ አትመልከት በቀላ ጊዜ፥ መልኩም በብርሌ ባንጸባረቀ ጊዜ፥ እየጣፈጠም በገባ ጊዜ። ³² በኋላ እንደ እባብ ይነድፋል፥ እንደ እፉኝትም መርዙን ያፈስሳል።
Mar 25, 2023