አንዴ ስሙኝማ ቤተሰብ እስከዛሬ ፍቅር ከያዘኝ ሰው ጋር ብቻ ካልሆነ በቀር የፍቅር ግንኙነትን ከሚወደኝ ሰው ጋርም ቢሆን ላለመጀመር ወስኜ ነበር ይሄን የወሰንኩት በምክንያት ነበር እናም ፍቅር ይይዘኛል በሚል ፍቅር ስለሚባለው ታሪክ እረስቼ ስራየን ና ትምህርቴን ብቻ መከታተል ጀመርኩ ሁለቱም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄዱ ነው ግን ያ ያሰብኩት ሀሳብ ሊሳካ አልቻለም በህይወት አጋጣሚዎቼ ውስጥ ብዙ ወንዶችን ባውቅም ልቤ ማንንም ሊያፈቅር ግን አልቻለም ለምን አልሆነም ብየ ከፈጣሪየ ጋር አልሟገትም በሌላ በኩል ደሞ ቁጭ ብሎ የማይጠብቅ እድሜ የሚባል ነገር አለ ይሄን ሁሉ የምለፋው የምማረው ደስተኛ ቤተሰብ ለመመስረት ነው ሁለት ወንዶች አሉ አፈቅርሻለሁ የሚሉኝ እውነቱን ለመናገር ለሁለቱም ከወንድምነት ባለፈ የፍቅር ስሜት የለኝም ግን እስኪ ከነዚህ ምርጫዎች የቱ እንደሚሻል በመንገር ተባበሩኝ 🙏 👉 ብዙ ሰው ፍቅር አብሮ በመኖር በመለማመድ ይመጣል ይላል ይሄ ነገር እውነት ይመስላችኋል ? 👉 ይሄ ለናንተ ሀሳቡ ትንሽ ሊከብድ ይችላል ለምን መቼም የማላፈቅረውን ሰው አግብቼ እሱም እኔም ደስታ ከምናጣ ከአንዱ ልጅ ወልጄ ብቻየን አልኖርም
Mar 23, 2023እኔም እንዳንቺ ነበርኩ እህቴ። እዚህ ላይ ሁሉ ከአመት በፊት ይመስለኛል ልቤ ድንጋይ ሆኗል ማንንም ማፍቀር አልቻልኩም ብዬ ፖስት አድርጌ ነበር። የማገኛቸዉ ወንዶች ሁሉ የልቤን አያደርሱልኝም።የማስበዉን አይነት ወንድ አይሆኑልኝም ነበር። እንዳንቺ ዉዝግብ ዉስጥ ነበርኩ። የተማርኩ፣ ቆንጆ፣ ስራ ያለኝ ነኝ ለምንድነዉ በዚህ ነገር ያልታደልኩት እል ነበር። እድሜዬም 30 ነዉ። ሁሉንም ነገር ትቼዉ መፀለይ ጀመርኩ። በአንድ አጋጣሚ ግን ከአንድ ሰዉ ተዋወኩኝ። እኔ ሌሎች እንዲሆኑልኝ እታገል የነበረዉን እሱ ግን እንዲ ብናረገዉስ ብሎ የሚጠይቀኝ ሆነ። አፍቃሪዬ እና ተንከባካቢዬ ሆነ። በቅርቡ እንጋባለን። አፈቅራለሁ ብዬ አስቤ የማላዉቀዋ ልጅ ተቀይሬ እያበድኩለት ነዉ። ልብሽ አንቺ ይሄ ነዉ ብለሽ መናገር በማትችይዉ ምክንያት ተቆልፎ ይቆያል። ፈጣሪ ይከፈት ላለዉ ብቻ ይከፈታል። የማትወጃቸዉን ወንዶች ለባልነት አታስቢያቸዉ። ህይወትሽ ይመሰቃቀላል። ጠይቂ ባል ከላይ ነዉ። ኦርቶዶክስ ከሆንሽ የፀገሮ እጨጌ ዮሀንስ ገዳም ሄደሽ ተሳይ። ባትሄጂም ካለሽበት ሆነሽ ተሳይ ፁሚ ፀልይ። መልስ ታገኛለሽ። እድሜዬ ሄዷል ብለሽ ማይሆን ዉሳኔ አትወስኝ። ምርጡን ሊሰጥሽ እና ሲሰጥሽ እንዳታበላሺዉ በጥበብ እንድትይዢዉ ስለፈለገ ነዉ ፈጣሪ ያቆየሽ።
Mar 24, 2023