የምናብ ጓድኛዬ ጋ በመለያየቴ እየጨነቀኝ ነው።😱😱😱😱 ትውውቃችን በሶሻል ሚዲያ ተጠንስሶ ወደ ስልክ አደገ፣ በየቀኑ ማውራት፣ ልክ በአካል እንደምንተዋወቅ ሆነን መተሳሰባችን ዳብሮ፣ አንድም ውሸት የሌለበት ደስ የሚል ፍቅር ውስጥ ገባን። እሷ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ለመሆን ቀናቶች ቀርተዋታል፣ እኔ በአንድ የመንግስት ተቋም ህክምና እያጠናሁ ነው። ከእለታት አንድ ቀን ለመገናኘት አሰብን፣ ምንም ከባድ ቢሆንም እሽ ተባባልን። ግን አልተሳካም።።😔😔😔 ሌላ ወራቶች አልፈው ለመገናኘት ተግባባን፣ ግን በአንድ ነገር ምክንያት መግባባታችን እንደ ጉም ተኖ ጠፋ።😖😖😖 እንደምትወደኝ ምንም አልጠራጠርም ግን አለመገናኘታችን ሽንፈት ሆነብኝ እናም ተዘጋጋን፣ ቀናቶች ነጎዱ፣ እኔም ዝም አልኩ። በዚህ መሃል ግን አንድም ቀን ሳላስባት አለማደሬን ሳስብ ምን ያክል እንደምወዳት ያለ እሷ ሁሉም ከባድ እየሆነብኝ እንደሆነ መረዳት አልከበደኝም ።እሷ ብርታቴ ነች ፣ ማንበብ ሲደክመኝ አይዞክ ምትለኝ፣ሲከፋኝ፣ ሲያመኝ እሷ ሁሌም በሃሳብ እኔ ጋ ነች። እናም ናፍቆቴ ሲብስብኝ ደወልኩ ፣ አታነሳም😔😔😔ቴክስት ፃፍኩ፣ ከዚህ በኋላ ሚቀየር ነገር የለም ህይወትህ ውስጥ አልገባም፣ ህይወቴ ውስጥ አትምጣ አለችኝ። ሁሌም ስለ ሷ ማሰብ ማቆም አልቻልኩም ምን ባደርግ ይሻለኛል? I know I hurted her!
Mar 23, 2023It seems like you made up a story😂😂 በዛ ላይ የmedicine student got no time to write this paragragh😂ያውም እንዲህ ኪነ ጥበባዊ በሆነ መንገድ😂
Mar 23, 2023