የአስቱ ተማሪ ነኝ እና አንዳንዴ ብቻዬን ማሳለፍ አዘወትራለው ይህን ነገር እና ከሰዎች ጋር ለመግባባት ምናምን ትንሽ ይቸግረኛል እና ጓጀኛኞት የማፈራበት መንገድ እና ጓደኛ የሚሆነኝ እፈልጋለው እንዴት ላርግ
Mar 22, 2023ከክፍልህ ልጆች ጀምር። በደንብ ተግባባ። ሌሎች ያንተን ባህሪ ሲያውቁ ይቀርቡሃል። በአንድ መንገድ ለብዙ ጊዜ የምትመላለስ ከሆነና በዛ መንገድ ባለፍክ ቁጥር የሆነ ሰው የምታገኝ ከሆነ ያን ሰው ሰላም እያልክ እለፍ። ይህ እኔ አድርጌው በጣም ውጤታማ የሆንኩበት መንገድ ነው። በዚህ ብቻ የልቡ ወዳጅ ያደረገኝ ሰው አለ። ጓደኛ ማብዛት የአላዋቂዎች መለያ ስለሆነ ጓደኛ አታብዛ። ኋላ አሁን ያለህበትን ብቸኝነት የሚያስናፍቅ ጓደኛም አትያዝ። ጥቂት የልብ ወዳጆች ይበቁሃል። ታድያ #የምትጠቅማቸውና #የሚጠቅሙህ ይሁኑ። በአንድ በኩል ብቻ ሲሆን ሚዛኑ ልክ አይሆንም።
Mar 23, 2023