በዚች አለም ምንም የሚያስደስተኝ ነገር ላገኝ አልሻልኩም፤ ሁሌ ይከብደጃል፤ ሀጥያት መስራትም ሰልችቶኛል። ቆይ አሁን እኔ ምንድነው መፍትሔዬ? ገዳም መሄድ ብፈልግም፤ወላጅ መተው አልሻልኩም፤ ጠዋት ተነስቶ ማስቀደስ እራሱ እኮ ይከብደጃል። ውጪ ከተዝናናው፤አሪፍ ምግብ ከበላውም ደስታዬ አይዘልቅም፤ ከእግዚአብሔር እንደራቁ ይሰማኛል፤ምቾት ሲበዛ መበደል ይመጣ የለ። እንዲ አርግልኝ ብዬ መፀለይ እራሱ አልደፈርም፤ ምክንያቱም እዚህ አለም ላይ ኖሮ አለመበደል ስለከበደኝ፤ ከፈጣሪ የሚያርቁ ብዙ ነገሮች ስላሉ። ንስሀ ነው ጥላ ከለላ የሆነኝ፤ ግን ታጥቦ ጭቃ መሆን ያበሳጫል። ኡፍ ምን ይሻለኛል፤ የቱ መንገድ ብጓዝ ነው ትክክል የሚሆነው አና ከፈጣሪዬ የማያርቀኝ። ስራ ባልገባ እና ቤተክርሰቲያን፣ ገዳማት፣ ፀበል እንዳልሄድ ደግሞ፤ መስራት ግድ ሆነብኝ። እስኪህ የእግዚአብሔር ሰዎች መላ በሉኝ።
Mar 20, 2023እህቴ አንድ ነገር ልምከርሽ በመጀመሪያ ለራስሽ የእርጋታ ግዜ ለመስጠት ሞክሪ ከዛን መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ሞክሪ ዝም ብለሽ በቀን የሆነ ያህል አንብቢ ብዙም አይደለም፡ ጸሎትም ሞክሪ ዝም ብለሽ 3-5 ደቂቃ ትናንሽ ጸሎትሽን ይሰማኛል ለምትይው እግዚአብሔር አቅርቢ።፡ከዛ በሂደት ነገሮች እየተስተካከሉ ይመጣሉ እመኚኝ በተለይ መጽሐፍ ቅዱስ ከ አዲስ ኪዳን ጀምረሽ አንብቢ። ቀስ በቀስ ደግሞ ከሰው ጋር መግባባት ሞክሪ ከመልካም ሰዎች ጋር ተገናኚ ከሰዎች ጋር ያለሽንም፡ግንኙነት መልካም ለማድረግ ሰዎች ለይ ብቻ interest ማሳየት ብቻ በቂ ነው perfect መሆን አይጠበቅብሽም።
Mar 20, 2023