ሰላም ሰዎች አንዴት ናችሁ ። 21 ወንድ ነኝ ። ገና በልጅነቴ 8 ክፍል እያለሁ የሆነች የክላሳችን ልጅን ትወድሀለች ትወድሀለች እያሉ ሙድ ሲይዙብኝ ሳለስበው ከሷ ፍቅር ያዘኝ ከዛ 12 ስንደርስ አነግራታለሁ ብዬ። ለራሴ ቃል ገባሁ ከዛ 9 ነኛ ክፍል ጨርሰን 10 ስንገባ አኔ ትምህርቴን ለማቋረጥ ተገደድኩ ።ከዛ ተለያየን ማለት መገናኘት አቆምን ምክንያቱም 6 ወር ያህል ፀበል ቦታ ነበርኩ። ከዛ ድኜ ትምህርቴን ቀጠልኩ አሁን ዘንድሮ university ገብቻለሁ። ከልጅቷ ጋርም አንድ UV ነው ያለነው። ነገር ግን ያኔ ልጅቷ ታሰየኝ የነበሩት ድርጊቶች ማለትም ጥላቻ እና ንቀት ዛሬም ጭንቅላቴ ውስጥ አለ። በዚህም የተነሳ ሴቶችን እጠላለሁ። ማፍቀር እፈራለሁ የሚገርመው ልጅቷን ዛሬም አፈቅራታለሁ። ልክ ሳያት ደስ ይለኛል ።በቃ አፈቅራታለሁ።ችግሩ እሷ አሁን ለሁለተኛ ግዜ ፍቅረኛ ይዛለች። ።አና እኔ ሴቶችን ለመጥላት ምክንያት የለኝም ።በጣም አንዳፈቀርኳት ስላወቀች በጣም ጠላችኝ ፍቅሬን አንኳን አንዳልገፅ ቅስሜን ሰባበረችው።የሆነ ቀን እውነቱን ልነግራት ተገናኝተን መንገድ ላይ ካንተ ጋር መታየት አልፈልግም (ታሳፍራለህ) አለችኝ። አስቡት :አኔ ማለት በሰፈርም በትምህርት ቤትም የጎበዝ እና የጨዋ ተምሳሌት ነኝ: በዛ ላይ ቆንጆ ነገር ነኝ ።ግን ይህንን ከተናገረችኝ ቡሀላ ፊቴን በመስታወት ማየት እፈራለሁ አና ሴት ብጠላ ለወሲብ ቤቻ ብመኝ ይፈረድብኛል?
Mar 19, 2023የተረገመች አንዳንድ ሴት ደሞ ቅጥ ታጣለች ተዋት ቀረህባት እንጂ አልቀረችብህም ለእንደዚህ አይነት ሰው ብለህ ሁሉንም አንድ አታድርጋቸው ህይወትህንም አታበላሽ
Mar 19, 2023