አስጠላኝ መኖር ደከመኝ ከምላችሁ በላይ በሽተኛ ሆንኩ አቅም አጣሁ በዛ ላይ ይሄን ሁሉ ስሜት መታመሜን መድከሜን መከፋቴን መደሰቴን የሚያውቅልኝ ሰው እንኳን የለኝም ታድያ ህይወት ምንድነው ትርጉሙ ????
Mar 17, 2023አዎ ይሰለቻል ! ይደክማል ! በሽተኛም ያደርጋል ! የሚያውቅልህ ቢኖር እንኳ ላይረዳህ (ጠብቆ ይነበብ) ይችላል። የሚረዳህ(ጠብቆ ይነበብ) ቢኖር እንኳ ሸክምህን ሊያቀል አይችልም። በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የሆንን ብዙ አለን። የምንኖረው ግን በተስፋ ነው። እናንተ ሸክማችሁ የከበዳችሁ ወደ እኔ ኑ እኔም አሳርፋችኋለው ላለን አባትና ጌታ ሸክማችንን እናራግፋለን። በመራራ ዓለም በጣፋጭ ፍቅሩ እንፅናናለን። ዓይናችን ወደ መስቀሉ አሻቅበን በዓለም ከመታወር ለመዳን እንጥራለን። ሕይወት ትርጉሙ ይኽ ነው። በሚታየው የማይታየውን መፈለግ። በግዙፉ ረቂቁን ለማየት መጣር። አይዞን !! ጥቂት ግዜ ነው።
Mar 17, 2023