ሌላው ሀገር እንዲህ ተራቆ፤ ኢትዮጵያ ግን ሳትዘምን የቀረችው ለምን ይመስላችዋል? ችግሩ የመንግስት ነው፤ የህዝብ ነው፤ ሀገሪቷ ናት.... ወይስ ሌላ አመለካከት ያላቹ ካላቹም ንገሩኝ እስኪ?
Mar 16, 2023ችግሩ የሁላችንም ነው። -የመንግስታት ችግር: ስልጣን ከያዙ ወዲህ ለሐገር እድገት ከመስራት ይልቅ የራሳቸውን ቤተሰብና፣ ብሔር በተለየ መልኩ መጥቀም። ሐገሪቱን ለማሳደግ እምብዛም ፍላጎት አለመኖር። ስልጣኑን ሲረከቡ ህዝብን ከህዝብ የመከፋፈል መንገድ በመጠቀም የስልጣናቸውን እድሜ ማርዘም። .... -የህዝብ (የኛ) ችግር: በተደጋጋሚ እዚህ ቻነል ላይ ይህን ጽፌያለሁ። አሁንም ልጻፈው.. እንደ እኛ ኢትዮጵያውያን ምርጥ መሪ ያገኘ ህዝብ የለም፤ እንደኛም እነዚህ መሪዎች ያባከነ ህዝብ የለም። የኢትዮጵያን ታሪክ ወደ ኋላ ሄደሽ በሙሉ ብታነቢ እኛ ያላመጽንበት ገዢ ወይም መንግስት የለንም። በኛ እድሜ እንኳ ብንመለከት በመለስ፣ በሀይለ ማርያም እና በአብይ ያመጽን ነን። መንግስታቱ ስህተት የለባቸውም ማለቴ ሳይሆን እኛ በተፈጥሯችን አማጺያን ነን። መንጌ፣ አጼ ሀይለ ሥላሴ፣ ልጅ እያሱ... እያልን ወደ ኋላ ወደ ዘመነ መሣፍንት፣ ዛጉዌ፣ አክሱም ሥርወ መንግስታት ስንሄድ ከሚኒሊክ በቀር (እርሱም ጠንከር ያለ ስለነበር፤ ግን አመጸኛ ነበር!) ገዢ በገዢ፣ ህዝብ በገዢ ሲያምጽ ነው የኖረው። እና በሰላም ተከባብሮ መኖር አይመቸንም። ሐገሪቷ ምን ታድርገን??? ከውሃ አልጎደለን አባይንና ሌሎች የአፍሪካ የውሃ ማማ ያስባለንን ውሃ ሰጠን። ከመልከዓ ምድር ከሞቃቱ ስምጥ ሸለቆና እሳተ ገሞራ እስከ ተራራማና ውርጭ የአየር ጸባይ ሰጠን። ከከተማ እስከ ገጠር የተመቸ መኖሪያ ሰጠን። መሬቷም ከ 45% በላይ ለግብርና የተመቸ አድርጎ ሰጠን። ለመብልም ለመጓጓዣም ታዛዥ እንስሶችን ሰጠን። ሰማያችን ዝናብ ሰጪ ምድራችን የተተከለን አብቃይ ነው። ከእንስሳትም ከእጽዋትም እንዳይሰለቸን በየአይነቱ ለያይቶ አሰማምሮ ፈጥሮ ሰጠን። በዚህስ ማመስገን ነው። የተሰጠንን በአግባቡ ተንከባክበን ከተጠቀምን ሌሎቹን የሚያስቀና በረከት ነው ያለን። ችግር ያለው ሰው ከሚባለው ፍጡር ነው። ሐሳቤ ነው።
Mar 16, 2023