sewoch bale tdar honen gn demo lijoch mewled banfelig eyechaln malet nw hatyat nw ende kehulum haymanoy antsar ngerugn beteley be Orthodox
Mar 15, 2023ልጅ ካልተፈለገ በጭራሽኑ ባያገቡ ይመረጣል ነገር ግን ግዴታ አይደለም። ቤተክርስቲያን ‟ለምን የማትወልደውን ፈታህ” ብላ እንጂ ‟ለምን አትወልድም?” እያለች አትወቀስም። ነገር ግን ጋብቻም ቅዱስ፣ ልደትም እርኩሰት እንደሌለባት ሐዋርያትም በቀኖናቸው የመሰከሩ በመሆኑ ልጅን ከመውለድ መሸሽ የለብንም፥ ቅዱስ ፍሬ ናቸው። ቤተክርስቲያን ጋብቻን ለ3 ምክንያቶች ነው የምታዝዘው። 1ኛ- ከዝሙት ጠንቅ ለመጠበቅ 2ኛ- የህይወት አጋርን/አጋዥን ለማግኘት 3ኛው- ዘርን ለመተካት ነው። ስለዚህ፥ አንድ ሰው በነዚህ 3ቱ ወይም ቢያንስ 2ቱን ቢያምን እና እስከ መጨረሻው አብረዋት ለመኖር ቢመኝ፤ ቢያገባት መልካም ነው። እንግዲ አንድ ሰው በጋብቻ ውስጥ በተፈጥሮ(መኻንነት) ወይም ያለተፈጥሮ ልጅ ላይወልድ ይችላል። መኻን ሆነው ማኅጸናቸው የተዘጉት እናቶቻችን እግዚአብሔር በምሕረቱ ማኅጸናቸውን ይክፈትላቸው እንላለን። ነገር ግን ያለተፈጥሮ (ሆን ተብለው) የሚደረጉ ጽንስን የመከላከል ዘዴዎች ከጥንት ጀምሮ እስከዛሬ የሚጠቀሙት ብዙኃን አሉ። ለምን መውለድ አልፈለጉም ለሚለው ብዙ ምክንያቶች:- 1) ፍትወቱን ብቻ በመፈለግ 2) እርጅና ወይ የአካል ቁመና(Shape) ልጠብቅ በማለት 3) የማሳደግ አቅም እጥረት 4) ያሉን ልጆች ይበቃሉ በሚለው እነዚህ እና የመሳሰሉት እንደ ምክንያት ይነሳሉ። ቤተክርስቲያን በዚህ ላይ አቋሟ ምንድነው ለሚለው። ሀ) ልጁ ሳይጸነስ ቀድሞ መከላከልን የምትከለከልም የምትፈቅድም አይደለም። ነገር ግን እንደ አውናን ግብሩን ወድዶ አብሮ መኖሩን መጥላት ግን አይቻልም። በዚህ ላይ በኢትዮጵያ ወጥ የሆነ ሥርዓት ባይወጣም የግብጽ ቤተክርስቲያን ግን ቅድመ ጸኒስ መከላከያን(contraception)ን በጉባኤ ሲኖዶስ መርምረው ተወያይተው ፈቅደዋል፥ የኛ እስካሁን ያሉት ነገር ባለመኖሩ የግብጹን እንደመማርያ ልንወስደው እንችላለን። 2) ነገር ግን የኛም ይሁን የግብጽ ፤ ሁሉም ባጠቃላይ እንዴ ከተጸነሰ ከሆነ ማውረድ አይቻልም። የእናት ሆድ አንዴ ጽንስ ከያዘ እና ሆዷ ከገፋ ያ ህጻን እንደ ድሮ ዘርፍሬ ሳይሆን ውስጣ ያለው ሰው ነው። ከዚህ በኋላ የሚያበጀው እግዚአብሔር እንደመሆኑ ያ በእናት ሆድ ያለው ትንሹ ቡቃያ ከጎልማሳው ነፍስ ጋር እኩል ነው። ስለዚህ ያን ጽንስ ማውረድ እንደመግደል ይቆጠራል። ባጠቃላይ፥ ስለትዳር እና ልጅ ያለው ይሄንን ይመስላል። ብዙ ሰዎች Childless marriage ይበሉ እንጂ እንዴ ትዳር ውስጥ ከገቡ ሰዎች በኋላ ጊዜያቸው በሄደ ቁጥር ስለልጅ ያላቸው ፍላጎት እየጨመረ እየጨምረ ይሄዳል።
Mar 16, 2023