ፍረሽ ተማሪ ነኝ እና ውጤት እስኪመጣ ቤት ስለምውል እተኛ ነበር አሁን በዛ ምክንያት መሰለኝ ከሰዓት(8-10am) ስሆን መማርም ሆነ ማንበብ ከብዶኛል እና ይሄን መጥፎ ልምድ እንዴት ልተወው እችላለሁ ?
Mar 15, 202330 ቀናት ቻሌንጅ ብለህ ፅፈህ 11 ሰዓት አላርም ሙላ፣ ስፖርት ወተህ ስራ፣ ቀዝቃዛ ሻወር ዉሰድ እና ቁርስ በልተህ ክላስ 2:30 እንደሚጀምር ሰዉ ተዘገጃጅ። ማታም በጊዜ መተኛት ከለመድክ እስከ 6 መቆየት ቻሌንጅ እራስህን አርግ። አላርም እዚህ ላይም ተጠቀም። ስትለምደም 7,8,9 እያልክ ትሄዳለህ። ኢንጂነሪንግ ተማሪ ነበርኩ ፍሬሽ ላይ እንቅልፍ አስቸግሮኝ ያበላሸሁትን ግሬድ 5ዓመት አፈር እየበላሁ አስተካክዬ ነዉ ተመርቄ የወጣሁት። የፍሬሽ ግሬድ ማለት ግቢ የመቆያህ ሚስጥር ነዉ። በፍፁም የፍሬሽን ግሬድ ተዘናግተህ ከ3.5 በታች እንዳታስወርድ። እንቅልፍህን ካሸነፍክ ታሳካዋለህ። መልካም ዕድል።
Mar 15, 2023