እንዴት አደራቹ ወንድም እህቶቼ፤ በጣም ወሳኝ መወያያ ርእስ መክፈት እንዳለብኝ እየተሰማኝ ነው። ከሁሉም ሀይማኖት ያላቹ ሀይማኖታቹን እየገለጻቹ በሚገባ እንድንረዳ አርጋቹ ጥያቄዎቹን እንድትመልሱ በትህትና እጠይቃለው። ከመልሳቹ ስለ ሀይማኖታቹ ለመረዳት ይጠቅመናልና። ሀ, የእግዚአብሔር /የአላህ ቃልን ጠብቆ እዚህ አለም የመኖር ሚስጥር ምንድነው?እስኪ ከምሳሌ ጋር አስረዱን? ለ, ያንተን/ያንቺን ፈጣሪ እንዴት ትገልጠዋለህ/ለሽ? ሐ, የመኖርህ/ሽ አላማ ምንድነው? እውን አሱን ነው እየኖርክ/ሽ ያለኀው/ሽው? መ, እራስህን/ሽ እንድትወድ/ጂ ያረገህ/ሽ ምንድን ነው? ለመልሳቹ ፈጣሪ ይስጥልኝ።
Mar 14, 20231)የፈጣሪን ቃል ጠብቆ የመኖር ሚስጥሩ #ሞት እንዳለብክ ማመን ነዉ።ከሞት በላይ ምንም ሊመክርህ አይችልም።ሞትን ብቻ ማሰቡ በቂ ላይሆን ይችላል #ከሞት #ቀጥሎ ደግሞ ስላለዉ ህይወትክ ስታስብ ይቺ ዱንያ ሺ ጊዜ ብታሸበርቅ ጠፊ መሆኗን ስትረዳ የፈጣሪህን ቃል ጠብቀህ ትኖራለህ። (ጠፊ መሆኗን ለመረዳት እሩቅ መሄድ አይጠበቅብኝም የቅርብ ግዜዉ የቱርኩ earthquake, ብዙ ሠዎችኝ የፈጀዉን ኮረና ማሰብ በቂ ነዉ) 2)የኔ ፈጣሪ በኔ ሚገለፅ አይደለም ግን እንደ እኔ የኔ ፈጣሪ አንድ የሆነ ያልወለደ ያልተወለደ እዉነተኛ አምላክ አንድ የሆነ የፍጥረታት ሁሉ አስገኚ ከጉድለት እና ከሰዉኛ ባህሪ ሁሉ የፀዳ ሀያል አዛኝነቱ ገደብ አልባ ፤የማይሞት ፤ፍጥረታቶቹን የሚረዝቅ፤ እያመፅኩት የሚምር ከትዕዛዙ ስዛነፍ የሚመልሰኝ አዛኝነቱ እንዲህ ነዉ ማይባል፤የሚንከባከበኝ ጠይቄዉ ማይነሳኝ...ወላሂ እንጃ ይሄ አይገልፀዉም እሱ ከዚ የላቀ ነዉ... 3)እኛ ሰዎችን አላህ ዱንያ ላይ ያስገኘን እሱን በብቸኝነት ልንገዛዉ ነዉ እንደ አጠቃላይ የሁላችንም አላማ ፈጣሪን ለመገዛት ነዉ የምንኖረዉ... የዚች አአለም አላማዬን ለራሴ ተዉልኝ 4)እራሴን እንድወድ ሚያደርገኝ ነገር እንደ እዉነቱ አላህ ወዶች #የተፈጥሮ ሀይማኖቴን ሳልለቅ እስካሁን መቆየቴ እራሴን እንድወድ ያደርገኛል።የአላህ ባሪያ መሆኔ እራሴን እንድወድ ያደርገኛል።የታላቁ ነብይ የነብዩ ሙሀመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)(የአላህ ሰላም በእሳቸዉ ላይ ይሁንሁንና)የእሳቸዉ ኡመት(ህዝብ) መሆኔ እራሴን እኝድወድ ያደርገኛል ሁሉንም spiritually ስናየዉ ያለዉን ነዉ የመለስኩልህ normally ከአለማዊ አንፃር አይደለም
Mar 14, 2023