አሁናዊዉ የኦሮሞው ነጉስ አብያችን አጨብጭበን እልል ብለን የሾምነውን ሰውየ ጨምሮ ጀሌዎቹ እነ ሁሉ ኬኛ አዲስአበባ ላይ ሌላውን ብሄር ለማፅዳት የሚያደርጉት ሴራ ሳየው ግርምም ድንቅም ይለኛል በ20ሚሊዮን ብር ለአዲስ አበቤያን ያስገባውና እነሱ እንደሚሉት ቅንጡ የተባለለት አውቶብስ ለካ ከደሀው ባለባጃጅ ጉሮሮ ተቀምቶ የተገዛ ነበር( ከባጃጅ ወደ ጋሪ ገብተናል ተመስገን ድንቄም ብልጽግና እድገት ወደኋላ ) የኑሮ ውድነቱን ጣራ ላይ ሰቅሎ የወጣቱን ስራ ቀምቶ በዚ በኩል ቤት ሰው ላይ እያፈረሰ ህዝቡን ቁምስቅሉን አሳጣው ከምስኪኑ ገበሬ ስንዴ በርካሽ እየወሰደ እሱ በጅ አዙር በዶላር ለውጪ ይቸበችባል ኤክስፐርት ማድረግ ጀመርን ብሎ ያወራው ምላሱ ስለቦረና ድርቅ መናገር አቃተው ያኔ በሰበቡ የተዘጋው ኢንተርኔት ምን ያህል ኢኮኖሚ እንደሚያዛባ ሳይገባው ቀርቶ አይመስለኝም እንደአለማቀፍ ያቺ ጀግና ጋዜጠኛ የሴቶች ቀን ላይ ስትሸለም እንደሀገር መሪነቱ የሆነ ነገር ማስተላለፍ ሲገባው ምንም አላለም ለምን ይሄን እናንተ መልሱት ግን ለምን ይሄ ሁሉ የገባችሁን አስረዱኝ ?? እውነት ይሄም ጊዜ ያልፍ ይሆን ከዘር የፀዳ ንፁህ ኢትዮጵያዊ መሪ ኢትዮጵያ ፈጣሪ ይሰጠን ይሆን እሱንም አላውቅም
Mar 12, 2023ከዘር የፀዳ አስተሳሰብ እንዲመጣ ከፈለግሽ ካንቺ ከራስሽ ጀምሪ። ጥያቄሽን የጀመርሽበት መንገድ አማራነት ፅድቅ ኦሮሞነት ደግሞ በተቃራኒው እንደሆነ አድርገሽ ነው የጀመርሺው። ከአንቺ ከእኔ እና ከግለሰብ ከሰፈር ከህዝብ ነው ለውጥ ሚጀምረው ያኔ ከላይ ያለው መንግስት ምንም አይነት ምርጫ አንኖረውም ቀጥ ለጥ ብሎ ይስተካከላል። እንዳንቺ አገላለፅ ከሄድን ግን ስለ አንዱ ብሄር ፃድቅነት ሌላውን ሰይጣናዊነትን አከናንበን ትርምስምስ እንዳልን ቆሽሽን መኖራችንን እንቀጥላለን። የድርጊቱ ባለቤት የኔ ብሄር ሰው ካልሆነ ድርጊቱ ምንም ይሁን ልክ አይደለም የሚለው የአስተሳሰብ ጨለምተኝነት ይመስለኛው ትልቁ የህዝቡ ችግር እና አዎንታዊነት። እኔ ድብልቅ ስሪት ነኝ ሁሉም ግን ንፁህ ኢትዮጵያዊ ሃበሻ።
Mar 13, 2023