ሰላም እንዴት ናችሁ? ኦሪት ዘዳግም ለምን ዘዳግም ተባለ? እና ወሳኝ የሚባሉ እና በሌሎች የኦሪት መጻሕፍት ላይ ሳይካተቱ በዘዳግም ብቻ የተጻፉ ሃሳቦች ምን ምን ናቸው?
Mar 06, 2023ትርጉሙም «ሁለተኛ ሕግ» ወይም «የሕግ ድግግሞሽ» ማለት ነው። ይህ ስም የሚያንፀባርቀው የኦሪት ዘዳግም አብዛኛው ክፍል እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በሲና ተራራ የሰጣቸው ሕግ የተደገመበትና ተስፋፍቶ የቀረበበት መሆኑን ነው። ሙሴ የመጨረሻዎቹን ቃሎቹን ለአዲሱ የእስራኤላውያን ትውልድ የተናገረው በዚህ በተስፋይቱ ምድር ጫፍ ላይ ነበር። እነዚህ የመጨረሻዎቹ የሙሴ ቃሎች በኦሪት ዘዳግም ውስጥ ይገኛሉ። ከዚያም ሙሴ የተስፋይቱን ምድር ከሩቅ አሻግሮ አይተ ሞተ። ምናልባት ዘዳግም ላይ ተለይተው የቀረቡት የሙሴ የመጀመሪያ ስብከት (ዘዳግም 1፡1-4፡43) የሙሴ ሁለተኛው ስብከት (ዘዳግ. 4፡44-28፡68) የሙሴ ሦስተኛው ስብከት (ዘዳግ. 29-33) የሙሴ ሞት (ዘዳግ. 34) Correct me if I'm wrong.
Mar 06, 2023