ሰዎች please ስለ ወራቤ UV ምታቁትን ጀባ በሉኝ ከአ.አ ስንት ሜትር ነው የስንት ሰአት መንገድ ነው አየሩ ውሀ መብራት wifi ምግቡ እንዴት ነው detail information ንገሩኝ please Tnx
Feb 26, 2023ወራቤ በተራራዎች መሐል የምትገኝ አስፋልት ተከትላ የተመሰረተች አየሯ ሞቃት የሆነች ከተማ ነች። ከመስከረም በኋላ ለ3 እና ከዚያ በላይ ወራት ቆዳን የሚያደርቅ፣ አቧራ የሚያለብስ እጅግ ሀይለኛ ነፋስ የሚተራመስባት፣ ከዚያም ለ4+ ወራት ልብ ድረስ ዘልቆ የሚሰማ አሰልቺ የጸሐይ ሐሩር የሚመታት፣ ከዚያም ወደ 4+ ወራት አሪፍ አንዳንዴሞ ከበድ ያለ ዝናብ የሚያገኛት ታዳጊ ከተማ ነች። የኢንዱስትሪ ከተማ በመሆኗ ዳቦ እና ዱቄት በሽ ነው። ከአዲስ አበባ 175 ኪሎ ሜትር የምትርቅ የ3+ ሰአት መንገድ አላት። ህዝቦቿ ስልጤዎች ሲሆኑ የከተማዪቱ መነጋገሪያ ቋንቋ ስልጥኛ እና አማርኛ ነው። አመዛኙ ህብረተሰብ የእስልምና እምነት ተከታይ ነው። ከተለያዩ ከተሞች ወደ ወራቤ የሚመጡ የሌላ ብሔርና እምነት ተከታይ ያላት ከተማ ናት። ሙስሊም ከሆንሽ መስጂድ በየቦታው ያለ ሲሆን አምስት ግዙፍ መስጂዶች ያሏት አሁንም በመገንባት ላይ ያሉ ትልልቅ መስጂዶች ሲኖሩ ክርስቲያን ከሆንሽ ከመናኸሪያው ጀርባ በሚወስድ ራቅ ያለ መንደር ቤተ ክርስቲያን ያላት፣ ጴንጤ ከሆንሽ በትክክል ልነግርሽ አልችልም። ወደ ዩኒቨርሲቲው መሄድ ከፈለግሽ ከአዲስ አበባ ወደ ወራቤ መጥተሽ መናኸሪያ ትወርጃለሽ። ከመናኸሪያው እንደወረድሽ ትወጪና አስፋልቱን ተሻግረሽ ባጃጅ ትዪዣለሽ። ባለ ባጃጁን "ዱና ሃያው መንገድ ላይ ወራጅ አለ።" ብለሽ ተሳፍረሽ ትሄጃለሽ። ወይም "ዱና ወራጅ አለ።" ወይም "ሃያው መንገድ ወራጅ አለ።" ማለት ትችያለሽ። ሁሉም አንድ ነው። አንዳንዴ "ዱና" ብቻ ካልሽው ከዩኒቨርሲቲው አሳልፎ ፋብሪካዎች መንደር ሊወስድሽ ይችላል። ነገር ግን ብዙ ጊዜ በዩኒቨርሲቲው መንገድ ላይ ነው የሚያቆምልሽ። ቀጣይ እንደወረድሽ አሁንም አስፋልቱን ስትሻገሪ አንቺን የመሰሉ በአካባቢው ባንክ ፍለጋ የሚርመሰመሱ ተማሪዎችን ትመለከቻለሽ። አለፍ ትዪና አዋሽ ባንክ ፊትለፊት ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚወስዱሽ ባጃጆች ጸሐይ እየሞቁና ድንጋይ እያሞቁ ተቀምጠው ታገኛለሽ። ተረኛው ላይ ገብተሽ ሲሞላ ወደ ዩኒቨርሲቲው ይወስድሻል። አረዘምኩት። ይቅርታ። ይህ ከከበደሽ ሴት ተማሪዎች እንዲቀበሉሽ አመቻችልሻለሁ። ለሌሎችም የቻልኩትን እተባበራለሁ።
Feb 27, 2023