ሰላም ቤተሰቦቼ 👋 እውነት ይህን ፅሁፍ ከብዙ እንባ ጋር ነው እየፃፍኩ ያለሁት......አሁን 16አመቴ ነው ከድሮ ጀምሮ ሽንቴን አንዳንዴ አልጋ ላይ እሸናለሁ(ያመልጠኛል) በዚህ ምክንያት አክስቴ ቤት ምናምን አላድርም ከቤተሠብም እየራኩ ነው እና እርዱኝ 😭😭😞
Feb 24, 2023አይዞሽ እህቴ ስሜቱን አዉቀዋለሁ....እኔም እስከ 11 አመቴ አካባቢ አልጋ ላይ እሸና ነበር ከአናቴ ጋር ዘመድ ቤት ስንሄድ በጣም ነበር የምትሳቀቀዉ የኔ የሚገርመዉ ደግሞ ለሊት ቀስቅሳኝ በግድ አሸንታኝ ተመልሼ እንደተኛሁ ወድያዉ ነበር የምሸናዉ.......ምናልባት ከጠቀመሽ እንዴት እነደተወኝ ልንገርሽ......ቀን ላይ ዉሃ ወይም ፈሳሽ ነገር ከጠጣሽ በኋላ ሽንትሽ ሲመጣ ረጅም ጊዜ ይዞ ለመቆየት ሞክሪ በተቻለሽ መጠን እስኪተዉሽ ድረስ ማታ አካባቢ በተለይ በተለይ ሻይ በፍፁም አትጠጪ.....እኔ እንደዚህ እያስደረጉ ነዉ ቀስ በቀስ ያስቆሙኝ አሁን ላይ ማታ ሽንቴን የመጨረሻ ወጥሮኝ እንኳን ብተኛ ለሊት ራሱ ተነስቼ አልሸናም አይረብሸኝም እናም የምመክርሽ ቶሎ ቶሎ መሽናትን መተዉ ነዉ....አይዞሽ ፈጣሪ ይረዳሻል!🙏🙏
Feb 25, 2023