አረ ወገን እኔ ጨነቀኝ እኮ ምንድነው እየሆነ ያለው ሀገራችን ላይ ' ምንድነው መጨረሻችን -የቦረናው እና የአንዳንድ አካባቢዎች የከፋ ድርቅ - በየሰአቱ አየናረ ያለው የኑሮ ውድነት - በአዲስ አበባ ዙሪያ በዘግናኝ ሁኔታ እየተፈፀመ ያለው ቤት ፈረሳ ጉዳይ የእናቶች ለቅሶ የልጆች መበተን የአንዳንዶቹ እራስን እስከማጥፋት የደረሰ ተስፋ መቁረጥ - ከየአካባቢው አየተፈናቀለ እና መግቢያ እያጣ ያለው ምስኪን ህዝብ..... ወዴት እየሄድን ነው ያለነው ?? የት ነው መጨረሻችን ? መንግስታችንስ እየሰራ ያለው ስራ ምንድነው ? እኛ ነን ያልተረዳነው ወይስ እሱ ነው ያልተረዳን ? ምን ማለት ነው ስንዴ ኤክስፖርት እያረጉ የስንዴ እጥረት አለ ማለት እኔ ግራ ገብቶኛል የገባችሁ ካላችሁ አስረዱኝ እስኪ?
Feb 23, 2023Bro ወደየትም አልሄድንም ከ ፈጣሪ ስለራቅን ነው.. ወደ እሱ ብንፀልይ እና ብንጮህ... ነው ሊስተካከል የሚችለው..🙏🙏🙏... ፈጣሪ ሀገራችንን ይጠብቅልን
Feb 23, 2023