የህግ ባለሙያዎች ወይንም ይህን ጉዳይ የምታውቁ ካላችሁ ምክር ፈልጌ ነበር። ከ4 ወራት በፊት መኪና ተጋጭቼ ነበር እናም ጥፍተኛው እኔ ስለነበርኩ የራሴን መኪና በራሴ ወጪ አሰራሁ ምክንያቱም በጊዜው የገባሁት የ3ተኛ ወገን ኢንሹራንስ ብቻ ስለነበረ። እኔ የገጨሁት መኪና ሙሉ ኢንሹራንስ የተገባለት በመሆኑ ይኅው ኢንሹራንስ መኪናውን ለማሰራት ከ400,000 ብር በላይ እንደፈጀ ሰማሁ። ይህንም የሰማሁት በሌላ አጋጣሚ መረጃው ደርሶኝ እንጂ ለኔ እስካሁን ተደውሎ አልተነገረኝም። አደጋ የደረሰበት መኪና ለማሰራት 400,000 ብር ይቅርና 100,000 ብር የሚሞላም ጉዳት አልነበረም። ነገር ግን አሁን ባሉት ዋጋ መኪናው ከተሰራ የኔ 3ተኛ ወገን ለዛ መኪና ሽፍን የሚሰጠው በህጉ መሰረት እስከ 100,000 ብር ብቻ ያለውን ነው ቀሪው ገንዘብ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ እንደሚከፍል ከሰዎች መስማት ችያለሁ። የእኔ ጥያቄ እውነትስ ይህን ቀሪ ገንዘብ ለመክፈል እገደዳለሁ? መኪናውን ለማሰራት ወጣ የተባለው ወጪ እጅግ በጣም የተጋነነ እና የሆነ የማጭበርበር ስራ እንደተሰራ ያስታውቃል ታዲያ ይህንን ያላግባብ የተጋነነ ወጪ ያወጣው ኢንሹራንስ እኔን በክስ ገንዘብ እንደከፍል ከጠየቁኝ ምን ማድረግ ይኖርብኛል? አመሰግናለሁ
Feb 17, 2023አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ያዢው ፕሮ ማክስ ሌቭል ብዬዋለሁ😅😅🙌🏾 አይዞሽ ግን አሁን ለምን እንቅልፍ የሚነሳህን ነገር ለራስህ ትሰጣለህ ሲመጣ ያኔ ፍርድ ቤት ሄደህ መካሰስ ነው እስከዛው ፈታ በል ብሮ አንዳንድ ነገሮች አሁን ላይ ምንም የማድረግ ቻንሱ ከሌለን ዘና ብለን እንኑን ባወጣው ያውጣው ብለህ (ፍርድቤትም ሰርቶ ይክፈል ቢልህ ነው አትስጋ እንደው ቢፈረድብህ እንኳን) ደሞ ለተንዛዛ የኢንሹራንስ ሂደት በትንሹ እኮ ከአመት እስከ 3 አመት ይፈጃል ፕሮሰሱ ኢንሹራንሱ ራሱ ከቨር ለማድረግ ስለዚ ተረጋጋ ኑሮህን ቀጥል ባለው ግዜ ይሆናል እንኳንም ከአደጋው አተረፈህ ብቻ አንተ እሱን አመስግን ፀልይ አለቀ #አዲዮስ!
Feb 18, 2023