Why does the Ethiopian Alphabet have 3 has? ሀ ሐ i dont know where the other one went.
Oct 01, 2020ሞክሼ የግዕዝ ፊደላት ሞክሼ ፊደላት የሚባሉት አንድ አይነት ድምጽ ያላቸው ነገር ግን በቅርጽ እና በስራቸው የተለያዩ ፊደላት የሆኑ ናቸው በድሮ ጊዜ ግን አባቶቻችን ሀን ከ ሐ ፣ ጸን ከ ፀ... ፊደሎችን በድምጽ አወጣጥ ይለዩአቸው ነበር። እነዚህ ፊደላት በቁጥር ፱(9) ሰሆኑ ሀ ፣ ሐ ፣ ኀ ፣ ሠ ፣ ሰ ፣ አ ፣ ዐ ፣ ጸ ፣ ፀ ናቸው። ሀ ➺ ሃሌታው "ሀ" ይባላል። ◦ሃሌ ሉያ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ስለሆነ ሃሌታው "ሀ" ተብሏል። ሐ ➺ ሐመሩ "ሐ" ይባላል። ◦ሐመር ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው በዚህ ፊደል ስለሆነ ነው። ኀ ➺ ብዙኀኑ "ኀ" ይባላል ◦ብዙህ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው። አ ➺ አልፋው "አ" ይባላል። ◦አልፋ ኦሜጋ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው። ዐ ➺ ዓይኑ "ዐ" ይባላል። ◦ዓይኑ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀምበት ስለሆነ ነው። ሠ ➺ ንጉሡ "ሠ" ይባላል። ◦ንጉሥ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለ ሆነ ነው። ሰ ➺ እሳቱ "ሰ" ይባላል። ◦እሳት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ስለሆነ ነው። ጸ ➺ ጸሎቱ "ጸ" ይባላል። ◦ጸሎት ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይሄን ፊደል ስለሆነ ነው። ፀ ➺ ፀሐዩ "ፀ" ይባላል። ◦ፀሐይ ብለን ስንጽፍ የምንጠቀመው ይህን ፊደል ነው። እነዚህ ሞክሼ ፊደላት አንዱ በአንዱ ቦታ መግባት የለበትም ምክንያቱም የትርጉም ለውጥ ያመጣሉ። ለምሳሌ ፦ ➺ ሠረቀ = ወጣ ሰረቀ = ሰረቀ ➺ አመት = አገልጋይ ዓመት = ዘመን ➺ ሰዐለ = ስዕል ሳለ ሰአለ = ለመነ ➺ መሀረ = አስተማረ መሐረ = ይቅር አለ ➺ ኀለየ = አመሰገነ ሐለየ = አሰበ ➺ ፈጸመ = ጨረሰ ፈፀመ = ነጨ ➺ ማኅሌት = ማመስገን ማሕሌት = ማሰብ @GeezMediaCenter Join 👇👇 https://t.me/joinchat/AAAAAEkSiWw7drZxpcxk4Q Comment @kokuha_haymanot_bot 💚 @kokuha_haymanot 💚 💛 @kokuha_haymanot 💛 ❤️ @kokuha_haymanot ❤️
Oct 02, 2020